በኢትዮጵያ የሚዲያ እና የሥነ ጽሑፍ ዘርፍ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ታዋቂው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ እና ገጣሚ መስፍን አራጌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
በ1965 ዓ.ም የተወለደው ጋዜጠኛ መስፍን አራጌ፣ ለሦስት አሥርተ ዓመታት ያህል በሙያው በታማኝነት እና በልዩ ትጋት አገልግላል።
በሥራ ዘመኑም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ደሴ ቅርንጫፍ፣ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎ እንዲሁም በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የደሴ እና አካባቢው ተወካይ በመሆን በጋዜጠኝነት እና በስቱዲዮ አስተባባሪነት የሕዝብ ድምፅ ሆነው ሠርተዋል።
በተለይም በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ አማካኝነት የደሴን እና የአካባቢውን ሁነቶች ለዓለም አቀፍ አድማጮች በማድረስ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ የነበረው ሲሆን፣ ከጋዜጠኝነት ሙያው ጎን ለጎንም በርካታ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎችን ለንባብ አብቅተል።
በተጨማሪም በደሴ ከተማ በተለያዩ የማኅበራዊ እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በነቃ ሁኔታ ይሳተፍ ነበር።ጋዜጠኛ መስፍን አራጌ ባልተጠበቀ ሕመም ምክንያት ሕይወቱ ያለፈው ከትላንት በስቲያ ነበር።
ባለ ትዳር እና የአንድ ልጅ አባት የነበረው ጋዜጠኛ መስፍን ነሐሴ 18/2018ዓም ከቀኑ 6:00 ሰዓት በደሴ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብሩ ተፈፀማል።

