የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ወደ ጅቡቲ አቀኑ

ግብፅ እና ኬንያ በትናንትናው እለት ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ግብፅ ከሱዳን ጋር ለ 6 ቀናት የሚቆይ ሁለገብ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ትናንት ጀምራለች፡፡

የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡

የፕሬዝደንት አል ሲሲ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት የፕሬዚዳንቱ የጅቡቲ ጉብኝት በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩም ነው ቃል አቀባዩ የገለፁት፡፡ በተለይም በፀጥታ ፣ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር የውይይቱ ዓላማ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም የግብፅና የጅቡቲ መሪዎች የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና ሀሳቦችን ለመለዋወጥም አቅደዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግብፅ እና ኬንያ በትናንትናው እለት ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት ዓላማ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር አካል ነው ተብሏል፡፡

ግብፅ ከኬንያ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ2021 በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ጋር ያደረገችው አራተኛ ስምምነት ነው፡፡ ከኬንያ በተጨማሪ ከሱዳን ፣ ከኡጋንዳ እን ከብሩንዲ ጋርም ግብፅ ወታደራዊ ስምምነት ፈርማለች፡፡

በተያያዘ ዜና ግብፅ እና ሱዳን በትናንትናው ዕለት ለ 6 ቀናት የሚቆይ ሁለገብ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በሱዳን ጀምረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት ወቅት የሚካሔደው ይህ ልምምድ ፣ የናይል ጠባቂዎች (Nile Protectors/ናይል ፕሮቴክተርስ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ከግድቡ በተጨማሪ ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ጉዳይም ከፍተኛ አለመግባባት ውስጥ የሚገኙ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe