“የግድቡን ጉዳይ ወደ ማይመለከታቸው የአረብ ሀገራት ለመውሰድ የሚደረገውን ጥረት አንቀበልም” ውጭ ጉዳይ

አዲስ አበባ የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች “አፍሪካዊ መፍትሔ” የሚለውን ሀሳብ ማድነቃቸው ተገልጿል፡፡

ከግድቡ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሱዳን የራሷ አጀንዳ እንደሌላት አምባ. ዲና ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ጉዳዩን ወደ ማይመለከታቸው የአረብ ሀገራት ለመውሰድ የሚደረገውን ጥረት አንደማትቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ ፣ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው ችግር በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈታ ኢትዮጵያ አሁንም ጽኑ ፍላጎት እንዳላትአንስተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ “ጉዳዩን ምንም ወደ ማይመለከታቸው ወደ አረብ ሀገራት ለመውሰድ የሚደረገውን ጥረት አንቀበልም” ብለዋል፡፡

በዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ መዲና ኪንሻሳ የነበረውን ድርድር በተመለከተ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአፍሪካ ሀገሮች አምባሳደሮች ገለጻ መደረጉን ያነሱት ቃል አቀባዩ ፣አምባሳደሮቹ አፍሪካዊ መፍትሔ የሚለውን ሀሳብ ማድነቃቸውንም ገልጸዋል፡፡

አሜሪካ፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከአፍሪካ ሕብረት እኩል ሚና ይኑራቸው በሚል ግብፅና ሱዳን የሚያቀርቡት ሀሳብ “አፍሪካ ችግሯን በራሷ እንዳትፈታና እንዳይሳካላት ለማድረግ ያለመ” መሆኑን ቃል አቀባዩ አንስተዋል፡፡ ካይሮና ካርቱም፣ ደቡብ አፍሪካ ከድርድሩ ታዛቢነት እንድትወጣ ፍላጎት እንዳላቸውም ነው ቃል አቀባዩ የገለጹት፡፡

ግብፅ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር በሆነችበት ጊዜ ብቻም ሳይሆን፤ ደቡብ አፍሪካ ሊቀመንበር እያለች እንዲሁም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አሁን ሕብረቱን እየመራች ባለችበት ወቅት የሕዳሴ ግድብን ጉዳይ ወደ ውጭ አካል ለመውሰድ እየተሞከረ መሆኑንም ነው አምባሳደር ዲና ያስታወቁት፡፡

አምባሳደር ዲና “በተለይ ወደኛ ቀርቦ ያለው ሃገር የራሱ አጀንዳ የለውም ፤ የሚያራምደው የሌላ አካል አጀንዳ ነው የምንለው ያለ ምክንያት አይደለም ፤ በተለይ ወታደራዊ ክንፉ የሌሎችን አጀንዳ ነው የሚያራምደው” ሲሉ የሱዳንን አካሄድ ተችተዋል፡፡

የሱዳን እና የኢትዮጵያን የድንበር ውዝግብ በተመለከተ ፣ ሱዳን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪ ሆና ሳለ ፣ ከድርጅቱ ደንብ ውጪ የኢትዮጵያን መሬት መውረሯ ተገቢ አለመሆኑን በመጠቆም ጫና እንዲደረግባት ኢትዮጵያ በመግለጫ ስለመጠየቋም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡ የኢጋድ ሊቀመንበር ሆና የቀጠናውን ሰላም አደጋ ላይ የሚጥል “ወረራ፣ ዝርፊያና ግድያ መፈጸሟ አሳዛኝ ነው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe