የጣልያን መንግስት እንግሊዘኛ ቋንቋን የሚጠቀሙ ዜጎቹን ለመቅጣት ያለመ ረቂቅ ህግ ይፋ አድርጓል

በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የሚመራው የጣሊያን መንግስት እንግሊዘኛ እና ሌሎች የውጭ ቃላትን በኦፌሴላዊ ንግግሮችና ዶክመንቶች ላይ የሚጠቀሙ ዜጎችን እስከ €100,000 ($108,705) ለመቅጣት ያለመ ረቀቅ ህግ ለታችኛው ምክር ቤት አቅርበዋል።

ህጉ ሁሉንም የውጭ ቋንቋዎች የሚያጠቃልል ቢሆንም፣ በተለይ በ”Anglomania” ወይም የእንግሊዘኛ ቃላት አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነው። ለፓርላማ ክርክር ገና ያልወጣው ረቂቅ በሁለቱም ምክር ቤቶች ከጸደቀ ህግ ሆኖ ይወጣል።

ረቂቁ ማንኛውም በህዝብ አስተዳደር ውስጥ ሹመት ያለው ዜጋ “በጣልያንኛ በመጽሐፍና በቋንቋው በመናገር የተካነ መሆን እንደሚገባው ይገልጻል። እንዲሁም በሀገሪቱ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች ውስጥ የሥራ መደቦች መጠሪያ አህጽሮተ ቃላትን ጨምሮ እንግሊዝኛን መጠቀም ይከለክላል።

በተጨማሪም የውጭ ድርጅቶች የውስጥ ደንቦቻቸው እና የሥራ ውሎቻቸው በሙሉ የጣሊያን ቋንቋን ማካተት እንደሚኖርባቸው ይደነግጋል።

በቀረበው ህግ መሰረት የሀገሪቱ የባህል ሚኒስቴር በት/ቤቶች፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ በንግድ እና በማስታወቂያዎች ላይ የጣሊያንን ቋንቋን እና ትክክለኛ አጠራሩን በትክክል መጠቀምን የሚከታተል ኮሚቴ ያቋቁማልም ተብሏል።

ምንጭ፦ CNN

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe