የጨጓራ ህመም ምንድን ነው?

የጨጓራ ህመም በሆድ እቃ ክፍል ደጋግሞ የሚከሰት የማያቋርጥ ቁርጠት ሲሆን ህመሙ ወደ ጎን ጥንት አካባቢ ጨምሮ ሊስማ ይችላል፡፡በእንግሊዘኛ መጠርያው ጋስትራይቲሰ ማለትም የጨጓራ ቁስለት ባሁን ሰዓት በሀገራችን አንገብጋቢ የጤና ችግር እየሆነ መቷል፡፡ በአጠቃላይ የጨጓራ ችን የላይኛው ሽፋን በተለያዩ ምክንያቶች መላጥ፤መጎዳትና መቁሰል ብለን ልንተረጉመው እንችላለን፡፡

ለጨጓራ ቁስለት/ህመም የሚያጋልጡ ነገሮች

የጨጓራ ባክቴሪያ በመባል የሚጠራው ኤች. ፓይሎሪ አንዱ የጨጓራ በሽታ መነሻ ነው ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ግድግዳን የሚያጠቃ ሲሆን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል
የተዛባ የእመጋግብ ስርአት
ለጨጓራ ጸር የሆኑ መድሀኒቶች NSAID,TB መድኃኒቶች…..
የጨጓራ ባክቴርያ በጨጓራችን ውስጥ መኖር
የሚያቃጥሉና የሚለበልቡ ምግቦች ማዘውተር
እርግዝና
ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት
ዕድሜ (የጨጓራ ግድግዳ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር እየሳሳ ይመጣል

· የመመገቢያ ሠአትን ጠብቆ አለመመገብ

የጨጓራ በሽታ ምልክቶች

የማቅለሽለሽ ስሜት
የሆድ ህመም
የሆድ መነፋት
ማስታወክ
የምግብ አለመፈጨት
የማቃጠል ወይም የማግሳት ስሜት በምግብ ሰዓት አካባቢ ወይም በማታ ሰዓት
ስቅታ(ስርቅታ)
የምግብ ፍላጐት መቀነስ
የደም ወይም የቡና ቀለም ያለው ትውከት
ጥቁር ቀለም ያለው ዓይነ ምድር ናቸው።

የጨጓራ በሽታ መፍትሄ ምንድነው?

ህክምና የሚሆነው በመጀመሪያ የጨጓራ ህመማችን ምን ዓይነት ምግቦች ስንመገብ ወይም ምን ዓይነት ተግባሮች ስናደርግ ሊነሳብን እንደሚችል ለይተን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡
ካፌይን ያላቸው መጠጦች (ለምሳሌ ቡና፣ ሻይ) አለመጠቀም
ሲትሪክ አሲድ ያላቸውን የፍራፍሬ ጭማቆዎች ( ለምሳሌ፦ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ወይን ወዘተ) አለመጠቀም
ሲጋራ ሚያጨሱ ከሆነ ማቆም
ከፍተኛ የቅባት/ፋት ይዘት ያላቸውን ምግቦች አይመገቡ
በፋይበር እና ፍላቮኖይድ የበለፀጉ ምግቦች ኤች. ፓይሎሪ የተባለውን የጨጓራ ባክቴሪያ ዕድገት ስለሚገቱ በጣም ጠቃሚ ናቸው ከነዚህ ምግቦች መካከል፦ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጐመን፣ የምግብ ማጣፈጫ ተክል፣ ጦስኝ፣ ሽምብራ እና አንዳንድ የሻይ ዓይነቶች ይጠቀሳሉ፡፡

እነዚህንና መስል ለጤናችን ተስማሚ የሆኑ ነገሮችን ብንጠቀም የጨጓራ ህመምን በቀላሉ ልንከላክል እንችላልነ. ሆኖም ግን ህመሙ የባሰና ልንቋቋመው ካልቻልን በአፋጣኝ ወደ ሃኪም ቤት መሄድ ይኖርብናል፡፡

የጨጓራ ህመምን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንችላለን?

1. ዝንጅብል!

– አነስተኛ የዝንጅብል ክፍል ወስዶ ከምግብ በፊት መውሰድ የምግብ ልመትን ያፋጥናል በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያን ያክማል፡፡

2. እርጎ!

– በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሠት የጨጓራ ህመም ተመራጭ ነው፡፡

3. ድንች!

– ግማሽ ብርጭቆ የድንች ጁስን በቀን 3 ጊዜ ምግብ ከመመገብ 15 ደቂቃ በፊት መጠጣት።

4. ቆስጣ እና ካሮት!

– የቆስጣ ጁስ እና የካሮት ጁስን በመደባለቅ መጠጣት።

5. ውሃ!

– በቀን ከ8-10ብርጭቆ ውሃ መጠጣት።

6. በፆም ወቅት ፍሬሽ የሆኑ የፍራፍሬ ጁሶችን መጠቀም ለምሳሌ ወይን ብርቱካን አፕል ፓፓያ…

7. ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ አለመመገብ ምክንያቱም ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ የምግብ ልመትን ስለሚያዘገይ ትንሽ ትንሽ ምግብ ሠአትን ጠብቆ መመገብ።

8. ሁል ጊዜ በባዶ ሆድ የሞቀ ውሃ መጠጣት።

9. በአንድ ገበታ ላይ የተለያዩ ምግቦችን አደባልቀው አለመመገብ።

10. ከመተኛቶ 2 ሠዓት በፊት እራት መመገብ።

11. በቫይታሚን ቢ12 እና አይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ።

12. ሥጋና የስጋ ተዋፅዎ መቀነስ በተለይ ለእራት አለመጠቀም።

13. አልኮል ሲጃራና ጫትን አለመጠቀም።

14. ቡናና ሻይ መቀነስ።

15. ኬክ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለመጠቀም።

16. በሀኪም ያልታዘዙ መድሀኒቶች አለመውሰድ።

17. ቅመማ ቅመም መቀነስ ናቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe