የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢሚኑኤል ማክሮን ” በዩክሬን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እያለሙ ነው” ተባለ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢሚኑኤል ማክሮን ወደ ዩክሬን ወታደራቸውን ሊያስገቡ ነው ተባለ።
‘ማክሮን በዩክሬን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እያለሙ ነው፤ አሁንም በታሪክ መዝገብ በወታደራዊ አዛዥነት ለመስፍር ተስፋ ያደርጋሉ ሲል የሩሲያ የውጭ ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።
በፕሬዝዳንቱ መመሪያ መሠረት የፈረንሳይ የጦር ኃይሎች ጄኔራል ኢታማዦር ሹም የኪዬቭ አገዛዝን ለመደገፍ እስከ 2 ሺህ የሚደርሱ ወታደሮችን እና መኮንኖችን ወደ ዩክሬን ለማሠማራት እየተዘጋጁ መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል።
የዚህ ኃይል ዋና አካል በዋናነት ከላቲን አሜሪካ ሀገራት የተመለመሉ የፈረንሳይ የውጭ ወታደሮችን ያቀፈ እንደሆነ የሩሲያ የውጭ ደህንነት አገልግሎት አክሏል።
“እነዚህ ምልምል ወታደሮች በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የፖላንድ አካባቢዎች ተሠማርተው ከፍተኛ የውጊያ ቅንጅት ሥልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe