የ”ፊንቴክ” የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

የ”ፊንቴክ” ኢንቨስትመንትን ሽፋን በማድረግ በተፈጸመ መጠነ-ሰፊ የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ ታዋቂ አርቲስቶች እና የቲክቶክ አንቂዎች ዛሬ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ፊት ቀርበዋል።
በእስር ላይ የሚገኘውን 5ኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማልን ጨምሮ፣ በዋስትና መብት በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን የሚከታተሉት ቀሪዎቹ ተጠርጣሪዎች በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው በጠበቆቻቸው አማካኝነት የክስ መቃወሚያ አቅርበዋል።
የ1ኛ ተከሳሽ ጠበቆች የ5 ገፅ፣ እንዲሁም የሌሎቹ ተከሳሾች ጠበቆች እያንዳንዳቸው ባለ 6 ገፅ የክስ መቃወሚያ ለችሎቱ ያስገቡ ቢሆንም፣ የቀረበለትን ሰፊ የክስ መቃወሚያ በዛሬው ዕለት ተመልክቶ ምላሽ መስጠት እንደማይችል አቃቤ ህግ ለችሎቱ አስታውቋል።
ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግን ጥያቄ በመቀበል፣ የቀረቡትን የክስ መቃወሚያዎች መርምሮ ምላሽ ለመስጠት ለሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Sourceሽገር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe