የፋሲካ ኤግዚብሽንና ባዛር በታላቅ ድምቀት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገለፀ

ከመጋቢት 23 እሰከ ሚያዚያ 7  ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚዘጋጀው  በሀበሻ ዊክሊ  ድርጅት ሲሆን በዝግጅቱ 300 በላይ ስመጥር የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሏል፤

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሸማቾች በሚጎበኙት በዚህ በአይነቱ ለየት ያለ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ የሀገርና የውጭ ሀገር ድርጅቶች የሚሳተፉበት በኢትዮጵያ ትልቁ ኤግዚቢሽንና ባዛር እንደሆነ ተነግሯል፤

ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን በስፋት ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ምዝገባ እያከናወኑ ሲሆን ምርቶች  በተመጣጣኝ በስፋት እንደሚቀርብ እና ልዩ ልዩ ሽልማቶች የሚያስገኙ ስጦታዎች እንደተዘጋጁ ሀበሻ ዊክሊ አስታውቋል ።

ሀበሻ ዊክሊ ከዚህ ቀድም የተዋጣለት የአውዳመት ኤግዚቢሽንና ባዛር በማካሄድ የሚታወቅ ድርጅት ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe