የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌባ መባሉን አስተባበለ፤

  • ዋና ኦዲተሯ ‹ሰራተኞቼን አምናቸዋለሁ ›ብለዋል፤

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ በፖርላማ ቀርበው ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከዳኞች አቃቤ ህግና ፖሊስ ቀጥሎ በሌብነት የተፊረጀው ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ፍረጃውን አስተባበለ፤

በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመው በፖርላማ ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ የፈፀሙት የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ከሙስና ጋር ተያይዞ ከምክር ቤት አባላት ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር አስተባብለዋል፤

ዋና ኦዲተሯ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፖርላማ ንግግር መስማታቸውን ጠቅሰው በማግስቱ በመስሪያ ቤታቸው እስከ ዳይሬክተር ባሉ የስራ መደቦች ላይ ካሉ የስራ ሀላፊዎች ጋር ስብሰባ መቀመጣቸውን ተናግረዋል፤

ዋና ኢዲተሯ እንዳሉት ከስብሰባው በኋላ አንዳንድ የስነ ምግባር ችግር የታየባቸው ኦዲተሮች ቢኖሩም አብዛኛው ኦዲተር በቅንነትና በታማኝነት ሙያቸውን የሚተገብሩ መሆናቸውን ከመግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፤

በመሆኑም ይላሉ ዋና ኦዲተሯ ‹ሰራተኞቼን አምናቸዋለሁ ›ብለዋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe