የፌዴራሉ መንግሥት የ2017 ጠቅላላ የወጪ በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል

የትሪሊየን በጀቱ ጉዳይ
የፌዴራሉ መንግሥት የ2017 ጠቅላላ የወጪ በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።
ለክልል መንግሥታት የበጀት ድጋፍ የተመደበው 236.7 ቢሊዮን ብር ነው።
አጠቃላይ የ2017 በጀት (971.2 ቢሊዮን) በ2016 በጀት ዓመት ከጸደቀው የወጪ በጀት አንጻር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው ተገልጿል።
ዛሬ ከሰዓት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ምክር ቤት ቀርበው በረቂቅ በጀቱ ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም ወቅት ሚኒስትሩ ከ971.2 ቢሊዮን የወጪ በጀት ፦
✔ 451.3 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ
✔ 283.2 ቢሊዮን ብር ለካፒታል
✔ 236.7 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት የበጀት ድጋፍ የተመደበ እንደሆነ አሳውቀዋል።
ለክልል መንግሥታት ከተመደበው ጠቅላላ የበጀት ድጋፍ ውስጥ 14 ቢሊዮን ብሩ የዘላቂ የልማት ግቦችን ለማስፈጸሚያ የሚውል ነው።
ከጠቅላላው የፌዴራል መንግሥት በጀት ከፍተኛውን ድርሻ (የጠቅላላውን 46.5 በመቶ) የያዘው ለመደበኛ በጀት የተመደው እንደሆነ የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ለመደበኛ ወጪ የተያዘው የበጀት ድልድል ሲታይ 127.2 ቢሊዮን ብሩ (28.2 በመቶ) ፦
° #ለአበል እና ለልዩ ልዩ ክፍያዎች ተመደበ እንደሆነ ተናግረዋል።
ቀሪው 321.4 ቢሊዮን ብር ለስራ ማስኬጅ የተመደበ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለመደበኛው ወጪ ከተደለደለው በጀት ለእዳ ክፍያ የተያዘው 139.3 ቢሊዮን እንደሆነም አመልክተዋል።
ለእዳ ክፍያ ከተያዘው ውስጥ 54.8 በመቶ ለሀገር ውስጥ እዳ ክፍያ ፤ ቀሪው 45.2 በመቶ ለውጭ ሀገር እዳ ክፍያ እንደሚውል ገልጸዋል።
ለፌዴራል መንግሥት ካፒታል በጀት የተመደበው 283.2 ቢሊዮን ብር ሲሆን የወጪ አሸፋፈኑ ሽፋን ሲታይም ፦
° 216.5 ቢሊዮን ብር ከትሬዠሪና ከመስሪያ ቤቶች የውስጥ ገቢ ፤
° 39.8 ቢሊዮን ብር ከፕሮጀክት እርዳታ
° 26.9 ቢሊዮን ብር ከፕሮጀክት ብድር ለመሸፈን የተያዘ እንደሆነ አብራርተዋል።
ከጠቅላላይ የካፒታል በጀት ውስጥ 187.1 ቢሊዮን ብር ቅድሚያ ትኩረት ለተሰጣቸው ፦
 ለመንገድ; ለትምህርት; ለግብርና እና መስኖ;መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን; ለጤና ለገጠር እና ከተማ ልማት ሴፍቲኔት ማስፈጸሚያ የተመደበ ነው ብለዋል።
በጦርነት ምክንያት የወደመውን ንብረት እና አገልግሎት ማስጪያ ተቋማትን ወደነበሩበት ለመመለስ እና ለማቋቋም ለተጀመረ ፕሮጀክት ከመንግሥት ትሬዠሪ ብድር 20 ቢሊዮን ተደግፎ መቅረቡን አሳውቀዋል።
የቀረበው ረቂቅ በጀት ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe