የፓርላማ አባላት የአየር ኃይል አባላትን እና ሠራተኞችን አወያዩ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቡድን አባላት የኢፌዴሪ አየር ኃይል የሠራዊት አባላትን እና ሲቪል ሠራተኞችን በተቋማዊ የሥራ ክንውን ዙሪያ አወያይተዋል፡፡

ቡድኑ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኙ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ተቋማት ባካሄደው የመስክ ምልከታ ወቅት ከአየር ኃይል አባላትን እና ሠራተኞች ጋር ተወያይቷል ፡፡

በውይይቱም በአካዳሚክ ዘርፍ ከሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎች እስከ አብራሪዎች ድረስ በየመድረኮቻቸው የተሳተፉ ሲሆን፤ የተቋሙ ሲቪል ሠራተኞችም በተዘጋጀላቸው መድረክ ተወያይተዋል፡፡

ባካሄደው ውይይትም የመጀመሪያ ደረጃ ግብረ-መልስ የሰጠ ሲሆን፤ በቅርቡ የተደራጀ የጽሑፍ ግብረ-መልስ እንደሚሰጥም ይጠበቃል፡፡

ከዚህም ባሻገር ከሰበሰባቸውን መረጃዎች በመነሳት ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ጋርም እንደሚወያይ የቡድኑ አስተባባሪ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት አመላክተዋል፡፡

የቡድኑ አባላትም የኢፌዴር አየር ኃይልን በሁሉም የሥራ ክፍሎች ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ላነሷቸው ጥያቄዎችም ከተቋሙ ሙያተኞች ምላሾች እንደተሰጣቸው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

SourceFBC
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe