የፖርቹጋል መንግስት ሚዲያዎችን ለመታደግ  ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ድጎማ ሰጠ

በኮቪድ 19 ሳቢያ በዓለም ዙሪያ ያሉ መገናናኛ ብዙሃን ስራቸውን ለማከናወን እየተቸገሩ እንደሆነ እየታየ ው፡፡ አንዳንድ የጋዜጦችና መፅሔቶች ዕለታዊና ሳምንታዊ ዕትሞቻቸን ማሳተም የተቸገሩ ሲሆን ራዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ለስራ ማስኬጃና ለሠራተኞች ደሞዝ የሚከፍሉት ከማስታወቂያ ገቢ ስለነበር ይህንን ለመሰብሰብ ባለመቻላቻው ከስርጭት ውጪ እየሆኑ ነው፡፡

Read also:የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎቹን በዚህ ዓመት እንደማያስመርቅ አስታወቀ።

ይህ ችግር በሀገራችን ሚዲያዎች ላይም በስፋት እየተስተዋለ ነው፡፡ መንግስት ምንም እንኳን በዚህ በኮቪድ ወቅት ሰራተኞችን መቀነስ አይቻልም የሚል አዋጅ ቢያወጣም አንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጣቢያውን ዘግቶ ሰራተኞቹን አሰናብቷል፡፡ የህትመት ውጤቶችም ሳምንታዊ ዕትሞቻችውን ወደ 15 ቀንና ወርሃዊ ለማድረግ ተገደዋል፡፡ ጨርሶውኑም ማተም ያቆሙ አሉ፡፡

Read also:የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ለበረራ አስተናጋጆች ለመስጠት የወሰነው  የቋንቋ ፈተና ተቃውሞ ገጠመው

ጉዳዮን በተመለከተ መንግስት የተቃዛቀዘውን የግሉን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ በብድር መልክ ለስራ ማስኬጃ መመደቡ የተነገረ ቢሆንም ከአበባና ከሆቴል ኢንቨስትምት ዘርፍ ውጪ የድጎማው ተቋዳሽ የሆነ የንግድ ዘርፍ የለም፡፡ የሚዲያ ስራ በወሳኝ ወቅት ለህብረተሰቡ መረጃ ማስተላላፍ ዋነኛ ስራቸው የሆኑት የመገናኛ ብዙሃን ከመቼውም በበለጠ መልኩ መረጃ ለህብረተሰቡ ማቅረብ በሚገባቸው ሰዓት በፋይናንስ እጥረት ሳቢያ ለመዘጋት እየተንገታገቱ ነው፡፡

Read also:በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ ላይ የተመዘገበው የባሌ ተራራሮች ብሔራዊ ፖርክ አደጋ ላይ…

የፖርቹጋል መንግስት ግን ይህንን ችግር ከግምት በማስገባት በሀገሩ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ለራዲዩዮና ለቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለጋዜጦችና ለመፅሔቶች እንዲሁም ለኢንተርኔት ሚዲያዎች የ11 ሚሊዮን ዩሮ ወይም  ከ350  ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ድጎማ ማድረጉ ተሰማቷል፡፡ ድጎማው መገናኛ ብዙሃኑ ሰራተኞችን ሳይበትኑና ስርጭት ሳያቋርጡ መረጃ የማድረስ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe