የ10 ወር ህፃን ለማገት የሞከረችው በ13 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣች

ወጣት ትዕግስት አለነ የተባለች ግለሰብ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ኤፍራታ የተባለ አካባቢ በቤት ሰራተኝነት ስራ ለመቀጠር በደላላ አማካኝነት ከአቶ ወርቁ ሰማ ቤት ከጧቱ 3:00 ገደማ ትገባለች።
ስራ ለመስራትም ከአሰሪዎቿ ጋር ተስማምታ መስራት ትጀምራለች።በዚሁ በመጣችበት ቀንም አሰሪዎቿ ሆኖን ወርቁ የተባለ የ10 ወር ህፃን ልጃቸውን አምነው ወደስራ ይሄዳሉ።
በቤት ውስጥ ከነበረው ከህፃኑ አጎት ስልክ በመለመን ወደማይሰራ የራሷ ስልክ ትደውልና ስልኩን ትመልሳለች ከዛም የህፃኑ አጎት ከቀኑ 9:00 ገደማ ከቤት ይወጣል።
ሰራተኛዋ ትዕግስት ግን አደራዋን በመብላት እና ያልተፈለገ ጥቅም ለማገኘት በማሰብ በዛው ስራ በጀመረችበት ቀን ከቀኑ 10:00 አካባቢ ሰው አለመኖሩን ካረጋገጠች በኋላ ህፃኑን ይዛ ትሰወራለች።
ቀጥሎም የህፃኑ ወላጆችና ዘመዶች ጉዳዩን ያውቁና አዳሩን ሙሉ ሲፈልጉት ያመሻሉ ግን ምንም አየን ወይም ሰማን የሚል ሰው አላገኙም።
በመጨረጫ ተያዘች ተፈረደባት
የባህርዳርና አካቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መስከረም 21 በዋለው ችሎት ትዕግስት አለነ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe