የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እርማት ላይ ቅሬታ ያቀረቡ የተማሪዎች ጥያቄ ውድቅ ሆነ!!

የትምህርት ሚኒስቴር   ለፖርላማው  ባቀረበው የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ የፈተና መሰረቅ መኖሩን አምኗል፤

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት  ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ የትምህርት ሚኒስቴርን የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚኒስቴር መስርያ ቤቱን እቅድ አፈጻጸም  አቅርበዋል፤

ሚኒስትሩ በዚህ ሪፖርታቸው  የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን  በተመለከተ ከበርካታ ተማሪዎችና ወላጆች  የቀረበውን አቤቱታ ተጨባጭነት ያለው አይደለም ብለውታል፤

ሚኒስትሩ ፈተና በመስረቅ ወይም ሂደቱን በማደናቀፍ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚጥሩ ኃይሎች መኖራቸውን በሪፖርታቸው የገለፁ ሲሆን በአንዳንድ አከባቢዎች  የተለያዩ ማማለያዎችን በማቅረብና ለስርቆቱ ፈታኙን ተባባሪ የማድረግ ሂደት ታይቷል ብለዋል፤

በፈተና ስርቆት የአከባቢው የመንግስት አመራሮች ጭምር እንደተሳተፉ የጠቆሙት የትምህርት ሚኒስትሩ ይህንን ሁኔታ ማስተካከል ካልቻልን በዚህ ክስተት ትውልድ ይመክናል ብለዋል፤

ከፈተናው እርማት ጋር በተያያዘ የቀረበው ጥያቄ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ተገቢው ማጣራት ተደርጓል ያሉት ሚኒስትሩ ካጋጠመው መጠነኛ ክፍተት በቀር የተማሪዎቹ ጥያቄ ውሃ እንደማያነሳ ጠቅሰው በሁኔታው ዙሪያ ከመግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፤

የተማሪዎቹና የወላጆች ጥያቄ በአግባቡ ምላሽ እንዲያገኝ ላቸው መግለጫ ያወጣው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እንዳለ ሀይሌ ሚኒስትሩ በፖርላማ ከመግባባት ላይ ደርሰናል ያሉት ከማን ጋር እንደሆነ ግልጽ እንዳልሆነላቸው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ገልፀዋል፤

የአማራ ክልል ተማሪዎችና ወላጆች፤ መምህራንና የአማራ ምሑራን መማክርት እንዲሁም የክልሉ ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች የፈተና ውጤት እርማት በድጋሚ እንዲታይ በተደጋጋሚ መጠየቃቸው ይታወሳል፤

የኢትዮጵያ ትምሕርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚፈጸመውን የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስርቆት ለመከላከል በቀጣይ አመት ፈተናውን በታብሌት ለመስጠት ማቀዱን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe