የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

በአጭር የፅሁፍ መልዕክት 8181 አማካኝነት የፈተናመለያ ቁጥር በማስገባትም ውጤት ማወቅ ይቻላል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆኗል። በመሆኑም ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

በድረ ገጽ ውጤት ለማየት http://result.neaea.gov.et የሚለውን በመጫን (ክሊክ በማድረግ) ይግቡ። ተማሪዎችም በፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እንዲሁም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ከዛሬ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ ማምጣታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት አስታውቋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተመዝጋቢ፣ በተፈታኝም እንዲሁም በውጤትም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55 ነጥብ 7 በመቶዎቹ ከ350 በላይ አምጥተዋል።

በመግለጫው የፈተና ውጤት ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ከ600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች 702 መሆናቸው ተገልጿል።

የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት 669 ሆኖ መመዝገቡንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።

የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ከ የካቲት 29 እስከ መጋቢት 2,2013ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe