የ30 ደቂቃ የሰውነት እንቅስቃሴ የማስታወስ አቅምን ያዳብራል – ጥናት

በቅርቡ የወጣ አንድ አዲስ ጥናት እንዳሳየው ከሆነ የ30 ደቂቃ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማስታወስ አቅምን እንደሚያዳብር ይፋ አድርጓል።

በርግጥ ከዚህ ቀደም የህክምና ባለሙያዎች ንቁ ጤናማና ረጅም ዕድሜ ለመኖር በሳምንት ቢያንስ ለ2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ያህል ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ባለሙያዎቹ እዚህ ላይ ሊደርሱ የቻሉት በመደበኛ ሁኔታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የአንጎል ህዋሳትን እንዲያድጉ ምክንያት በመሆኑ ነው ብለዋል።

አሁን በአሜሪካ ሜሪይላንድ ዩኒቨርስቲ ይፋ የተደረገው አዲሱ ጥናት ታዲያ ለ30 ደቂቃም ቢሆን እንቅስቃሴ ማድረጉ በአዕምሮ ክፍል ላይ የአሰራር ለውጥ ማምጣት እንደሚችል አሳተዋል።

በአሁን ወቅት በዓለም ዙሪያ በተለይም ዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች በመርሳት በሽታ የመያዝ ዕድላቸው እየሰፋ እንደመጣ ይነገራል።

ታዲያ እንዚህን መሰል ጉዳዮች ለመከላከል ዕድሜን ግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲዘወተሩ በህክምና ባለሙያዎች ይመከራሉ።

ምክንያቱ ደግሞ አዕምሮ ነገሮችን ቶሎ እንዳይረሳ የማነቃቃት አቅም ስለሚፈጥርለት ነው ብለዋል።

ምንጭ፡ ሜይልኦንላንን ጠቅሶ ፋና ቢሲ ዘግቦታል

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe