የ50 ሎሚ ጥሪ

የ50 ሎሚ ጥሪ
*************
ጋዜጠኛ ታምራት ኃይሉ የ ” ቁም ነገር ” መጽሔት መስራችና ዋና አዘጋጅ ነው ። ” ቁምነገር ” በኪነ ጥበብ እና በማህበራዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረግ ላለፉት 22 ዓመታት ስትታም ቆይታለች ። በመጽሔቷ ላይ ከ1000 በላይ እንግዶች ቃለመጠይቅ ተደርጎላቸው ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ ሲያደርግ ከ450 በላይ ወጣትና አንጋፋ ደራሲያን እና ጋዜጠኞች የብዕር ትሩፋታቸውን ለአንባቢ እንዲያቀርቡ ዕድል ፈጥሯል፡፡ በቁም ነገር መጽሔት ላይ ተከታታይ ጽሑፎቻቻውን ያቀረቡ ደራሲያን ጽሑፎቻቸውን ሰብሰበው ወደ መጻሕፍት ጥራዝ እንዲቀይሩ ታምራት በቀና ተባባሪነት ብዙዎችን አግዟል፡፡ አበረታቷልም፡፡ ዛሬስ?ዛሬ ደግሞ ተራው የእርሱ ሆኗል፤ ” ዜሮ ዓመት የሥራ ልምድና ሌሎች ወጎች ” የተባለ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ለመጽሔቷ ቤተሰቦች የቅድመ ሕትመት ግዢ አቅርቧል ። የህትመት ዋጋ የማይቀመስ በሆነበት በዚህ ጊዜ የ50 ሎሚን ይትበሃል መከተል አስፈላጊ ነው።
የመጻሕፍቱ ዋጋ ፦
የአንድ መጽሐፍ ዋጋ ብር 275:00
የ4 መጽሐፍ ዋጋ ብር 1,000:00
የ8 መጽሐፍ ዋጋ ብር 2,000:00
የ12 መጽሐፍ ዋጋ ብር 3,000:00
የ20 መጽሐፍ ዋጋ ብር 5,000:00
የ40 መጽሐፍ ዋጋ ብር 10,000:00
የ60 መጽሐፍ ዋጋ ብር 15,000:00
የ80 መጽሐፍ ዋጋ ብር 20,000:00
የ100 መጽሐፍ ዋጋ ብር 25,000:00
ዝቅተኛው መግዛት የሚቻለው ብዛት 4 ይሆናል ።
የመጽሐፉን ዋጋ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000563013145 ለታምራት ኃይሉ ትራንስፈር አድርጎ ስክሪን ሾቱን በ0911232015 ላይ በቴሌግራም መላክ ይችላሉ። ወይም የሚከተለውን ሊንክ በመጫን በቀላሉ መክፈል ይችላሉ።
መጽሐፉ እንደታተመ በየአድራሻዎ የሚላክ ይሆናል።
በጋዜጠኝነት ዘመኔ ተወዳጅ እና በወቅቱ አነጋጋሪ የነበሩ ቃለመጠይቆችን የሰራሁት በቁም ነገር መጽሔት ላይ ነው ። በመሆኑም ይህን ዘመቻ ለማስጀመር የብር 5,000:00 መጽሐፍ ለመግዛት ብሩን በተገለጸው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ አድርጌያለሁ ። 5 መጻሕፍትን ለእኔና ለ4 ወዳጆቼ ከወሰድኩ በኋላ 15ቱ ለተለያዩ ቤተ መጻሕፍት እንዲሰጡ እደርጋለሁ ። የ ” ቁምነገር ” ቤተሰቦች ( በመጽሔቷ ላይ ቃለመጠይቅ የተደረገላችሁ ፣ የጻፋችሁ ፣ የመጽሔቷ የንባብ ደንበኛ የነበራችሁ ) በወጣው ዝርዝር መሰረት አጋርነታችሁን እንድትገልጡ ጥሪ ቀርቦላችኋል ። (ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe