ግለሰቦቹ መሐመድ ቃሲም የተባለን የ9 ዓመት ታዳጊን ጨዋታ ላይ በነበረበት ጊዜ ቦታ እንዲያሳቸው በማግባባት ይዘውት በነበረው መኪና እንዲገባ በማድረግ ይዘውት ይሰወራሉ፡፡
ሰይፈዲን ሺፋ እና ዳንኤል ጌቱ የተባሉት ግለሰቦች ታዳጊውን በመኪናቸው ከወሰዱት በኋላ በአንድ ሆቴል ውስጥ በማስቀመጥ ከቤተሰቦቹ ጋር ገንዘብ መደራደር ይጀምራሉ፡፡
ልጃቸውን እንዲያገኙ 3 ሚሊዮን ብር እንዲያዘጋጁ የታዳጊው ቤተሰቦች ይነገራቸዋል ይህን የማያደርጉ ከሆነ ልጃቸውን በህይወት እንደማያገኙት በመግለጽ፡፡
ወላጆቹ ያላቸውን ንብረት በመሸጥና በመስጂድ ወስጥ ከሰዎች ብሩን በማሰባሰብ ይሞላላቸው እንዴት እንደሚከፍሉ አጋቾችን ሲጠይቁ የሚላክላቸው የራይድ መኪና ስላለ ገንዘቡን በጥሬ እንዲሰጡ ይጠየቃሉ ይህንንም ያደርጋሉ፡፡
በዚህ መሠረት ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ አጋቾቹ ልጁን ከወሰዱበት ቦታ ይመልሱታል፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን አባት የራይዱን ታርጋ ፎቶ አንስተውት ስለነበረ በተደረገ ክትትል ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግለሰቦቹ ላይ የ11 ዓመት እና የ ዓመት 10 እስራት እንደፈረደባቸው ተሰምቷል፡፡//

