” ዩክሬን በቅርቡ NATOን የምትቀላቀልበት ምንም መንገድ የለም ” – ቦሪስ ጆንሰን

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ሀገራቸው ዩክሬን የNATO ወታደራዊ ጥምረትን ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ልታቋርጥ እንደምትችል ሀሳብ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ይህንን ሃሳባቸውን ተከትሎም የብሪታንያው ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን ለሚዲያዎች እንደተናገሩት ዩክሬን በቅርቡ NATOን የምትቀላቀልበት ምንም መንገድ እንደሌለ እና ይህም ለሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ግልፅ እንደተደረገ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ” ወደፊት ግን ውሳኔው ለዩክሬን ዜጎች እና ለተመረጠው መሪዋ (ቮድሚር ዜሌኒስኪ) የተተወ ነው ፤ እኛ ግኝ እንደግፋቸዋለን ” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ዜሌኒስኪ ከሩስያ ጋር የተኩስ አቁም እና ሩስያ ጦሯን ከዩክሬን እንድታስወጣ ለማድረግ ድርድር እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ሩስያ በዩክሬን ላይ ምታካሂደው ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም ከተፈለገ በዋነኝነት ካስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ዩክሬን NATOን እቀላቀላለሁ የምትለውን ሀሳቧን እርግፍ አድርጋ እንድትተው እና ገለልተኝነቷን እድታረጋግጥ የሚል ነው።

ሩስያ፤ ዩክሬን ለሀገሯና ለህዝቧ በምንም መልኩ ስጋት እንደማትሆን እስካላረጋገጠች ጊዜ ድረስ እርምጃዋን እንደምትቀጥል ነው እየገለፀች የምትገኘው።

ዩክሬን የNATO ጥምረትን ለመቀላቀል ለዓመታት ስትታገል ቆይታለች፤ ነገር ግን ይህ እርምጃዋ ሩሲያን በእጅጉ አስቆጥቷታል፤ ሩስያ በአጠገቧ ሌላ የNATO አባል ሀገር ፈፅሞ ማየት አትፈልግም።

[ በሌላ መረጃ ፦ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ነዳጅ ፍለጋ የገልፍ ሃገራትን ጎብኝተዋል። እንደ ስካይ ኒውስ መረጃ ዛሬ በዩኤኡ እና ሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል። ]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe