ሰሞኑን በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተስተዋሉ ላሉ ግጭቶች መባባስ ብሎም ወጣቶችን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እየመራቸው ያለው
ማህበራዊ ሚዲያው በዋናነትም ፌስ ቡክ በመሆኑ ‹አስፈላጊው ትኩረት ሊደረግበት ይገባል› የሚሉ ንግግሮችን በመንግስት ባለስልጣናት ሲነገር
እየሰማን ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩም በተለያዩ አጋጣሚዎች ተመሳሳይ ንግግር ሲያደርጉ ተደምጧል፡፡ ንግግሩ በግርድፉ ሲታይ በሰሞኑ በኦሮሚያና
በአንዳንድ የአማራ ክልሎች የተነሳውን ግጭትና ተቃውሞ የሚመራው ማህበራዊ ሚዲያው በመሆኑ አንድ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል የሚል
አንድምታ አለው፡፡ ማህበራዊ ሚዲያ ሃሳብን በነፃነት የመግለጫ አንዱ መንገድ ተደርጎ በመላው ዓለም ተቀባይነትን ያገኘ የመገናኛ ብዙሃን ዘዴ
ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡
እርግጥ ነው ማህበራዊ ሚዲያዎችን በአግባቡ ባለመጠቀም የሚመጣ ፍጅት እንዳለ ማንም አይጠፋውም፡፡ ለዚህ ግን መፍትሔው
ማህበራዊ ሚዲያዎችን ማፈንና መንግስት የሚፈልገው ብቻ እንዲፃፍበት ማድረግ ሳይሆን ሌሎቹን በህግና በሀላፊነት ላይ የተሰማሩ የመገናኛ ብዙሃንን መደገፍና ማበረታታት ነው፡፡
በሀገሪቱ የነበሩትና ምዝገባ አውጥተው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የግል የመገናኛ ብዙሃን የተለየ ሃሳብ በማንፀባረቃቸው ብቻ በልዩ ልዩ መንገድ
ከህትመት ውጪ እንዲሆኑ መደገረጉና ያሉትም በወረቀት ዋጋና በህትመን መናር ሳቢያ እየተንገዳገዱ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ ፊቱን ወደ ማህብራዊ ሚዲያዎች በተለይም በወደ ፊስ ቡል ቢያዞር የሚገርም አይደለም፡፡
ነፃና ግልፅ ሚዲያ እንዲዳብርና እንዲጠነክር መንግስት በተለያዩ መድረኮች ላይ የግል የመገናኝ ብዙሃንን በማስታወቂያ ለመደገፍን ፓሊሲ
እያረቀቅሁ ነው የሚል ተደጋጋሚ መስጠቱን እናስታውሳለን፡፡በመሆኑም መንግስት ይህንን መግለጫወን ትቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊገባ ይገባል፤ ያን ጊዜ ሃላፊነት በሚሰማቸው የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱ ዜጎች ድምፅ እንዲሰማ በማድረግ የዲሞክራሲያዊ ስርዓቱ እንዲዳብር
ማድረግ ይቻላል፤ አለበለዚያ ግን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እጅን በመቀሰር ችግሩን መፍታት እንደማይቻል ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
ያን ሲያማ ያን ሲያማ ወገኔ ለእኔ ብለህ ስማ – ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ
