” ይሄ ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ስላከበራችሁኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ” – እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)

እጅግ ተወዳጇ አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተበረከተላትን የክብር ዶክትሬት በተመለከተ መልዕክት አስተላልፋለች።

ምን አለች ?

እጅጋየሁ ሽባባው ፦

” እምዬ ሀገሬ ፤ ውድ ሀገሬ ኢትዮጵያ እንዲሁም በጣም የምወዳችሁ የማከብራችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ሰላም ሰላም ብያለሁ።

በአክብሮት የሰጣችሁኝን የአክብሮት ዶክትሬት በጣም በትልቅ ደስታ ነው የተቀበልኩት ፤ በጣም አመሰግናለሁ፤ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እኔ በጣም በጣም ነው የገረመኝ ታጭቼ ብገኝ እንኳን የሚያስደንቀኝ ነበር ተመርጬ ስለተነገረኝ በጣም ነው የማመሰግነው፤ እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

ፍቅራችሁ እንዲሁ አክብሮታችሁ ስለሆነ በእኔና በወገኖቼ ስም እንዲሁም በዚህ ሁሉ ደስ በሚላቸው ኢትዮጵያውያን ስም ከልቤ በጣም በጣም አመሰግናለሁ።

እግዚአብሔር ህይወታችሁን ይባርከው ፣ የኢትዮጵያ ዛሬ ያሉትን #ተማሪዎች እንዲሁም የወደፊቱን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ፣ ሀገራችንን መንፈስቅዱስ ይጠብቅልን።

ያስቸግራል ለመግለፅ ደስታዬን ፤ በጣም አመሰግናለሁ፣ ፍቅራችሁና ክብራችሁ ከልክ ያለፈ ነው ፤ ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ይሄን ሁሉ ስላከበራችሁኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

የኢትዮጵያን ህዝብ እግዚአብሔር ይጠብቅልን ፤ ምስጋናዬ በጣም ከፍ ያለ ነው፤ በአካል ተገኝቼ አንድ ቀን እዛ መጥቼ አያችኃለሁ ፤ በሰላም ቆዩኝ ይሄንን አጭር መልዕክቴን ይቅር በሉኝ ፤ በደንብ አድርጌ ሌላ ቀን አመሰግናችኃለሁ ፤ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እጅጋየሁ ነኝ “

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe