ይህ ሞትን ንቆ ሞትን ራሱን ያስበረገገ ሰው ከፊል ታሪክ ነው !!

ይህ ሞትን ንቆ ሞትን ራሱን ያስበረገገ ሰው ከፊል ታሪክ ነው !!

ይህ የሀገርንና የቤተሰብን ሀላፊነት በደሙ ፍሳሽ በአጥንቱ ክስካሽ ለመጠበቅ ዘብ የቆመ ሰው ቁንጽል ማስታወሻ ነው !!

ይህ ህይወቱን ገብሮ ሀገር በክብሯ እና በማዕረጓ ህዝቦቿ በአንድነትና በሰላም እንዲኖሩ ለመታደግ የታገለ የአንድ ሰው ሽራፊ ታሪክ ነው!!

ሁለት ራሱን ሆኖ የመቶዎችን ጥይት የተቋቋመ ሀገሩ እንዳትቆሽሽ ህዝቡ እንዳይዋረድና እንዳይሰቃይ በነፍሱ የተወራረደ የጀግንነትን ሚዛን የደፋ የእሸቴ ሞገስ አጭር ታሪክ ነው።

ባለፉት ሰሞናት በሰሜኑ የሀገራችንክፍል የተሰራጨው የሽብር ደዌ የበረታ ፈተና አስከትሏል።

ማን ለሀገሩና ለህዝቡ እንደቆመ ማ በልቡ ታምኖ በጀግንነት ሰገነት ላይ እንደተውጣጣ ምርቱን ከግርዱ ለይቶ አሳይቷል።

እሸቴ ሞገስ አሁን በቃል ልናነጋግረው በአካልም ልናየው አንችልም። ግን ለሀገሩ ክብር የከፈለው የህይወት ዋጋ ያሳየው ጀግንነት አብሮን አውሎ አብሮን ያሳድረዋል ተወላጆቹንም የክብር ታሪክ መጎናጸፊያ ያጎናጽፋቸዋል።

ህዳር 17/2014 ዓ/ም ሸዋሮቢትንና ሳላይሽን እሸቴ ሞገስንና የአሸባሪውን የህውሀት ታጣቂዎችን አገጣጥሟቸዋል።

እሸቴ ሞገስ የ56 አመት ጎልማሳ ነበር በቀውት ወረዳ ማፉድ ሳርአምባ አካባቢ ነው የተወለደውና ያደገው ከትውልድ ቦታው ቅርብ በሆነችው ሸዋሮቢት ቤት ሰርቶ ቤተሰብ መስርቶ እያረሰና እየነገደ ይኖራል።

የህውሀት ታጣቂዎች ወደ ሸዋ ሮቢት እስኪደርሱም ድረስ ከከተማው ሰው ጋር ተግባብቶና ተከባብሮ ሲኖር ነበር።

ቁመቱ የተዘናጠፈ የሚባል ረጂም አቋሙ የተስተካከለ ጠይም ዝምታንና ኮስተር ማለትን የሚመርጥ ነበር ይላሉ ቤተሰቦቹ።

ትጥቅ አሳማሪ ነው እንደ ብዙዎቹ የአካባቢው ሰዎች ዝናር በወገቡ የታጠቀው ጠመንጃ በትክሻው የያዘው ገና የ15 አመት ታዳጊ በነበረበት ጋዜ ነው። አሁን በጎልማሣነቱም ጊዜ የክላንሽኮቭ ጠመንጃ ታጥቋል።

በህዳር ወር መጀመሪያ ህውሀት ለጥፋት ያሰማራቻቸው ታጣቂዎች ከሚሴን አልፈው ወደ አጣዬ ተጠጉ ያን ጊዜ ጀምሮ እሸቴ በሚታወቅበትና ቃሉ በሚደመጥበት የሸዋ ሮቢት ከተማ ነዋሪውን ከማስተባበር አልቦዘነም አካባቢያችንን አናስደፍራትም በሬሳችን ላይ ካልሆነ ሸዋሮቢትን አናሳልፈውም እያለ ሲያስተባብር ቆይቷል።

በሸዋሮቢት ውጊያ ሆነ እሸቴም ከልጁ ጋር ሆኖ ተዋጋ ግን ለጊዜው አሸባሪዎቹ አይለው ሸዋሮቢትን ያዙ እሸቴ ሞገስ ከግቢው ምሽግ ሰርቶ እዚሁ ተዋግቼ እሞታለሁኝ እንጂ አላፈገፍግም ብሎ ሞገደ።

እናቱ ካሉበት ድረስ ተጠርተው ” በአጠባውህ በጡቴ ” ብለው ለምነው ሸዋሮቢትን አስለቀቁት እሸቴ ያን ጊዜ ከልጁ ከይታገስ እሸቴ ጋር ሆኖ ከሽዋሮቢት በስተምስራቅ በግምት 15 ኪሎ ሜትር ወደ ምትርቀው ሳላይሽ ሄደ ።

ሳላይሽ የዘመዶቹ አካባቢ ነውና አሰፋ ታዬ ከሚባለው ዘመዱ ቤት ደረሰ።

የህውሀት ታጣቂዎች ሳላይሽን ተሰራጩባት እሸቴ ያንን ቦታ ትቶ እንዲያፈገፍግ ተመከረ ያን ጊዜ ግን አሻፈረኝ አለ !!

አፈግፍጌ የት ልደርስ ነው? ለአካባቢያችንስ እኛ ካልተዋጋንለት ማን ይመጣል ? አለ

ይህ ቃሉ የማሽረውና የማይገስሰው ቁርጠኛ ኪዳኑ ነበር የህውሀት ታጣቂዎች እሸቴ ያለበትን ቤት ከበቡት ብዙ ናቸው ግን ብዛታቸው አላስፈራውም

“አንድ አንበሳ እኮ ነው ሽላም አስደንባሪ ”

የሚለውን ብሒል አስቦ ሊሆን ይችላል የ ክላሹን ቃታ ሞልቅቆ ጥይቱን አቀባበለ ልጁ ሽጉጡን መዘዘ ተኩስ ተከፈተ ምድር ቀውጢ ሆነች አካባቢው በጥይት ታረሰ።

እሸቴ ሞገስ ወትሮም ድር ይበጥሳል የማባል ተኳሽ ነበር ይላሉ ጥይት ያለ መላ አይተኮስም ከሚሉት ተኳሾች ጋር የሚወዳደር ነበር።

እያነጣጠረ ተኮሰ አምስቱን ግንባራቸውን እየነደለ ጣላቸው ተኩሱ ሲበዛበት ከነበረበት የአሰፋ ታዬ ግቢ ወጥቶ በማሽላ ውስጥ ገባ ያን ጊዜም ልበ ሙሉ እንደሆነ ነበር ሞት ከፊቱ ሲያገጥበት ወግድ አለው እንጂ አልፈራውም ።

በእዚያ የጭንቅ ሰአት ተረጋግቶ ለእህቱ ባል ስልክ ደወለ።

እሸቴ ሞገስ በጠላቶቹ ምሽግ ከበባ ውስጥ ሆኖ ህዳር 17/20 14ዓ/ም ከኑነ 8:30 ለይ ያስተላለፈው መልዕክት

“ሳላይሽ አፋፈ ታዬ ቤት ውስጥ መሽገን ከበቡን አሁን ይሄን የምነግርህ እኛ እየሞትንነው እንድታስተላልፍልን ነው አሰፋ ታዬ ቤት ውስጥ ኔነ አምስቱን ይታገሱ አንዱን በሽጉጥ ገደልናቸው ከእዚያ እኔ ከገደልኩት ለይ ጠመጃ ማርኮ እንደገና ሁለቱን ደገማቸው ሲበዛንነ ወደ ኋላ አፈገፈግንና በላኋ በር ወደ ላለ ግልብጥ ስንል ተንደርድረው ሲመጡ ሁለቱን ደገምኳቸው እኔ 9 ገለናል ቅዱስ ሚካኤል ምስክሬ ነው።”

እሸቴ እና ልጁ 9 አሸባሪዎችን በጥይት እንደረፈረፏቸው ቅዱስ ሚካኤልን ብሎ ምሎ ተናገረ።

ወደ ማሽላው እርሻ ሲገባ ልጁ ይታስሰ በጥይት ተመቶ ህይወቱ አለፈ የመጀመሪያ ልጁ ይታገስ እሸቴ በ31 አመቱ ጠላቶቹን እየተፋለመ በአባቱ አጠገብ ወደቀ። !!

አባት የልጁ አስከሬን አጠገቡም ተዘርግቶም የሚያስበው ገድሎ ስለመሞቱ እንጂ ስለመኖሩ አልነበረም።

በልጁ አሟሟት ሳይሆን በልጁ ሞት ሊያለቅስ ሞከረ ግን ለጀግና እንደማይለቀስ ሲገባው ወዲያው ተወው እርሱም ገድሎ ለመሞት ቆርጧል የስልኩን ንግግሩን ቀጥሏል ንግግሩ ጎሽ ሰብሮ እንደያዘ አንበሳ እንጂ ለመሞት የተቃረበ መሆኑን ያረጋገጠ ሰው ድምጽ አይመሥልም ነበረ።

የሰልክ ልውውጡ

“አዳምጠኝ ይታገስን ገደሉብኝ ይሰማሀል በደንብ ያዝልኝ የሞተው የትጋ መሠለህ እኔም አሁን ከሬሳው ጋር ነኝ ከበውኛል እዚያው ነው የምሞተው አሰፋ ታዬ ቤት ከታች በኩል የእሱ ማሽላ አለ በኋለኛው በር ሬሳችን እዚያ ነው የሚሆነው መዝግብ በኋላ ይሄን በሰማይ ነው የምከፍልህ 9ኙን ገለን እኛ በመጨረሻ ወደማሽላው ስንንሸራተት መቱብኝ አላለቅስም ግን ብቻችንን እኔና እሱ ብቻ ”

በጀግንት ባለደፈርም ባይነት ጠላቶቹን ከፊቱ የጣለው እሸቴ ሞገስ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ቢመከርም እንቢ አለ !!

“እኔ ሬሳ እየጠበኩ ነው ወደ ኋላ አልልም አላፈገፍግም እዚያው ነው የምሞተው”

ለጠላት ጀርባዬን አላሳይም አለ ከስልኩ ምልልስ በኋላ ስንቶቹን እንደገደለ ምንስ እንደተፈጠረ የሚያውቁት ገዳዮቹ ብቻ ነበሩ በኋላ እንደተረጋገጠው ከእዚያ የስልክ መልዕክት በኋላ በሸጥና በፈፋ መካከል እየተወረወረ ተዋጋቸው ጥይቱ መሬት ማመታርፈው እሸቴ ሞገስ ጠላቶቹን ደጋግሞ ሳይጥል እንደማይቀር የታመነ ነው።

ራሱን ብቻ ሆኖ ትተረየስንና ስናይፐር ዲሽቃና ላውንቸር ከያዙት ጠላቶቹ ጋር ለሰአታት ተፋለማቸው ጥይት መተካት አይችልም በብዙዎችም ተከቧል ለማምለጥም አይፈልግም።

እሸቴ ሞገስ ወደቀ !!

በኋላ እንደተረጋገጠው ወደፊት ሳዋጋ ከኋላ ተሹለክልልከው የመጡ አሸባሪዎች ጥይታቸውን አፈሰሱበት ለሀገሬ ክብር ለህዝቤ ሰላም ለቤተሰቤ ጽናት ግንባሬን እሰጣለሁ ያለው እሸቴ ሞገስ ቃሉን ጠብቆ ደሙን አፈሰሰ።

የጀግንነትን እና የክብር ሞትን ለትውልድ መማሪያ እንዲሆንም በደማቅ ቀለም ጽፎ አለፈ !! እሸቴ ሞገስ ለሀገሩ ክብር ህይወቱን ለመስጠት በመዘጋጀቱ ኢትዮጵያን የመጠበቅ ሀላፊነቱን ተወጣ።

የልጄን አስከሬን ትቼ አልሄድም በማለቱም የአባትነት ታማኝነቱን በእዚያ ጭንቅ ሰአትም አረጋገጠ !! በእዚያች ሰአት ሌላ ነገር ይቀረው ነበረ ቀሪ ቤተሰቦቹስ ታዳጊ ልጆችም አሉት ከሞት ጋር በተፋጠጠበት በእዚያ ጊዜም ልጆቹን አልረሳየውም ስለዚህም እንዲህ ብሎ አደራ ሰጠ።

“ሌላውን አዳምጠኝ የቀሩት ልጆቼ ማሳደጊያ መኪና እዚሁ ሊቃጠል ነው ያው እነሱ ስለሚያውቁት ያቃጥሉታል ለመንግስት አሳውቅልኝና ልጆቼን አደራ ልጆቼ ርሀብ እንዳይሞቱብኝ አደራ ለመንግስ አሳውቅ”

ጀግንነቱን ለሀገር ልዕልና ያዋለው እሸቴ ሞገስ አደራውን ሰጥቷል ህይወቱን የሰጠው እኛ ቋሚዎቹ የተወረወረብን ቋጥኝ እንዳያጎብጠን ቀና ብለን እንድንሄድ ነው ብሎ ነው፤ ከተመረዘ የሽብር አየር ወጥተን የሰላም አየር አንደንተነፍስ ብሎ ነወ።

እናም አደራው ምቾታችንን እንዳይሸራረፍብን ለሌውወ መሥዋዕትነት ከብረንና አጊጠን ለመኖር ለምንፈልገው ሁሉ መሆኑን አያከራክርም አደራውበየጦር ግንባሩ የአሸባሪዎችን ቃትቀ ለመመከት ለህዝባቸው አንድነትና ለሀገራቸው ሰላም ሲሉ በየግንባሩ የወደቂትን ጀግኖች ሰዎች ጭምር እንድናስብ የሚጎንጠን ነው።

የእሸቴ ሞገስ ገድልም የብዙ የመከላከያና የልዩ ሀይል የፋኖ የሚሊሻና የፖሊስ አባላት ገድል ነው።

የጠላታቸውን ጉሮሮ ፈልቅቀው የአሸባሪዎችን ግንባር በርቅሰው ህይወታቸውን የሰጡንን ጀግኖቻችንን ሚዘክርና ዝንታለም የሚወደስ ተመሣሣይ ታሪክ አላቸው።

ሀገር የምትድነው የምትተላለፈውም ሞትን በናቁ ጀግኖቻይን ነው። ጀግናም ምንጊዜም ሞተ አይባልም ክብር ለጀግኖቻችን ።

***

ቤተሰቦቹን ለማግኘት የምትፈልጉ ዶ/ር ይተብት ሞገስ (ወንድም)

09-12-86-55-84

( በ #sheger 102.1 ሬድዮ የቀረበው የእሸቴ ሞገስ እና የልጁን የጀግንነት ታሪክ የሚተርከው ሙሉ ፅሁፍ ) እሸቴ አሰፋ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe