ይልቅ ወሬ ልንገርህ፡- የፖርላማ አባለት የመኪና አደጋ አጋጠማቸው

ዛሬ ጠዋት ለመስክ ምልከታ ወደ አማራ ክልል ሲጓዙ የነበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ደብረብርሃን አቅራቢያ ይጓዙበት የነበረው መኪና ከሌላ መኪና ጋር በመጋጨቱ ጉዳት መድረሱ ተሰማ፡፡ በዚህም ሳቢያ ዛሬ ጠዋት በሶስት ሰኣት መጀመር የነበረበት የፖርላማው ስብሰባ በአንድ ሰዓት ዘግይቶ የተጀመረ ሲሆን አደጋው የደረሰባቸው የምክር ቤቱ አባላት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው የህክምና እርዳታ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እየተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል፤ አደጋው ከደረሰባቸው ሰዎች መሀከል ሁለቱ ብቻ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሌሎቹ ቀለል ያለ ህክምና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ተጎጂዎችን ለማየት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄደው እስከሚመለሱ ድረስ የምክር ቤቱ ስብሰባ ዘግቶ ሊጀመር ችሏል፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe