ዮቶፕያ የፋሲካ ኤግዚቢሽንና ባዛርን በሚሊንየም አዳራሽ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት ይካሄዳል

ሀበሻ ዊክሊ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 07 ቀን 2015 ዓ/ም ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት ፤ ዮቶፕያ የፋሲካ ኤግዚቢሽንና ባዛርን በሚሊንዬም አዳራሽ ያዘጋጃል።
ታላላቅ የንግድ ትርዒቶችን በጥሩ ስነ ምግባር እና በስኬት በማዘጋጀት መልካም ዝና ያካበተው ሀበሻ ዊክሊ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 07 ቀን 2015 ዓ/ም ፤ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ ዮቶፕያ የፋሲካ ኤግዚቢሽንና ባዛርን በታላቅ ድምቀት ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዛሬ በሚሊንዬም አዳራሽ ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግመጫ ላይ ገልፆል።
ከሦስት መቶ በላይ ስመጥር የአገር ውስጥና የውጭ ኩባኒያዎች በሚሳተፉበት ፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሸማቾች በሚጎበኙትና በሚገበያዩበት በዚህ ደማቅ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ልዩ ልዩ ድርጅቶች ፤ አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እና ምርቶቻችውን ለብዙሃን እንዲሸጡ አዘጋጁ የአክብሮት ግብዣ አቅርቧል።
በተንጣለለው ሚሊንዬም አዳራሽ በድምቀት በሚካሄደው ዩቶፕያ የፋሲካ ኤግዚቢሽንና ባዛር በተጨማሪ ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦቶሞቲቭ ፣ ሪል እስቴት እና ባንኮች በጋራ ተገናኝተው ከልዩ የበዓል ቅናሾች ጋር የሚሳተፉበት ልዩ የንግድ ትሪዒት እንዲሁም ብራይዳል ሾው እና የስራ ፈጣሪዎች ሰፊ ቦታ መሰናዳቱም ተገልፃል ፡፡
በሚያዘጋጃቸው ኤግዚቢሽንና ባዛሮች ላይ አዳዲስ ነገሮችን በመፍጠር የሚታወቀው ሀበሻ ዊክሊ በዮቶፕያ የፋሲካ ኤግዘቢሽንና ባዛር ላይ በሚሊኒዬም አዳራሽ ከወተሮው የተለየ ድንቅ ክስተቶችን እንደሚያስተናግድና ለጎብኝዎችም በመግቢያ ቲኬት ለእድለኛ ጎብኚ ልዩ ልዩ ሽልማቶች ለማበርከት ከወዲሁ መዘጋጀቱን ሀበሻ ዊክሊ አስታውቋል ።
ከዚህም በተጨማሪ በአፍሪካ የመጀመሪያው የዳይኖሰር ጁራሲክ ትእይንት ፤ ልጆች ዘና የሚሉበት የማቆያና የጨዋታ ቦታ ፤ ነጻ ዋይፋይ አገልግሎት እንዲሁም በየዕለቱ ከኤግዚቢሽንና ባዛሩ ጎን ለጎን አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ አርቲስቶች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት በጉጉት የሚጠበቁ ትዕይንቶች እንደሆኑ ተነግሯል ።
በርካቶች በጉጉት በሚጠብቁት በዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ለመሳተፍ ቀድመው ለሚመዘገቡ ድርጅቶችና ተቋማት 20% ቅናሽ እንደሚያገኙ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe