ደረጃቸውን ያላሟሉ የለስላሳ መጠጦችና የታሸጉ ውሃዎች ከገበያ እንዲወገዱ ተደረገ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጃር ውሃን ጨምሮ የለስላሳ መጠጦች የተቀመጠውን ደረጃ ሳያሟሉ ለገበያ መቅረባቸውን በተደረገ ክትትል መታወቁን ገልጻል፡፡

ምርቶቹን ለገበያ ባቀረቡት ነጋዴዎች ላይ ፍቃዳቸውን ከማገድ አንስቶ በወንጀል እስከመጠየቅ የደረሰ እርምጃ መወሰዱን ተናግሯል፡፡ የንገድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ የተመረቱ እና ከውጪ የገቡ የተለያዩ ምርቶች የተቀመጠውን አስገዳጅ ደረጃ ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባለሙያዎችን በገበያ በማሰማራት ቁጥጥር ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል፡፡

በዚህ የቁጥጥር ስራም ከተቀመጠው ደረጃ በታች የሆኑ የተለያዩ ምርቶች ተገኝተዋል፡፡ ከምቶቹ መካከልም የአርማታ ብረት፡የልብስ ሳሙና፡የለስላሳ መጠጦች እና የጃር ውሃ ይገኙበታል መባሉን ከሸገር ሬዲዮ ዘገባ ላይ ተመልክተናል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe