ዳሸን ባንክ የሴት ሠራተኞቹን አቅም ይበልጥ ለማጎልበት የሚያስችል መርሃ-ግብር አስጀመረ

ዳሸን ባንክ የሴቶችን የመሪነት ሚና ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል መርሃ-ግብር በዛሬው እለት አስጀምሯል፡፡
መርሃ-ግብሩ ባንኩ ሁሉም ሰራተኞች ዕኩል ዕድል የማግኘትና የማደግ አጋጣሚ እንዲያገኙ ለማድረግ ካለው ራዕይ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው ተብሏል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋናስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ “ዛሬ የምንኮራባቸው የአገራችን ታሪካዊ ድሎችን እንድንጎናፀፍ ሴቶች ከፍተኛ አስተዋፅዎ አበርክተዋል” ብለዋል፡፡
በታላላቅ አገራዊና ተቋማዊ ስኬቶች ጀርባ የሴቶች ሚና የጎላ ነው ያሉት አቶ አስፋው ሴቶች ተገቢው ዕውቅና ሊሰጣቸው አንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ዳሸን ባንክ ይህን ክፍተት በአግባቡ ተገንዝቦ የሚሰራ በመሆኑ ከምስረታው ጀምሮ ሴቶችን በከፍተኛ የአመራር ዕርከኖች ላይ በመሾም ወደፊት በማምጣት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
ዳሸን ባንክ ሴቶችን በአግባቡ ያካተተ አሰራር በመፍጠር አዳዲስ ፈጠራዎችንና ውጤታማነትን እንደሚያጎለብት ተመላክቷል፡፡
በዳሸን ባንክ የሠው ሐብት ዋና መኮንን ወ/ሮ ህይወቴ ከፈለኝ በበኩላቸው “ፕሮግራሙ በባንካችን ለወደፊት ከፍተኛ አመራር መሆን የሚችሉ ሴቶችን ከወዲሁ ለመለየትና ለማብቃት የተነደፈ ነው” ብለዋል፡፡
በተጨማም የተሻለ ልምድ ያላቸውን ሴቶች ድጋፍ ከሚሹ ሴቶች ጋር በማገናኘት ጠቃሚ የሙያ ዕድገት እንዲያገኙ የሚረዱ ድጋፎችን ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe