ዳሽን ባንክ ለኤሌጋንስ ድርጅት 50 የኤሌክትሪክ መኪኖችን በወለድ ነፃ ፋይናንስ አቀረበ

​ዳሽን ባንክ በከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱ (ሸሪክ) አማካኝነት ለኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ድርጅት የመጀመሪያ ዙር 50 የቢ.ዋይዲ (BYD E2) የኤሌክትሪክ መኪናዎችን በፋይናንስ ማቅረቡን አስታወቀ።

​እነዚህ መኪኖች በያንጎ የትራንስፖርት ሥርዓት አማካኝነት ለሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚውሉ ሲሆን፣ የአካባቢ ጥበቃን ያገናዘቡና የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያስፋፉ መሆናቸው ተገልጿል።

የጉዞ ክፍያዉም በዳሽን ሱፐር አፕ በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚፈጸም ተጠቁሟል።

​የባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ አምዱ ሰማን እንደገለጹት፣ ሸሪክ በአሁኑ ወቅት ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለ ሲሆን፣ ከተሰበሰበው 30 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ውስጥ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነውን ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በፋይናንስ መልክ አቅርቧል።

​የኤሌጋንስ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቶፊቅ መሐመድያሲን በበኩላቸው ለተደረገላቸው የፋይናንስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ ከባንኩ ጋር ያላቸውን አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe