ዳሽን ባንክ ” ዱቤ አለ” የተሰኘው በተራዘመ የክፍያ ጊዜ ግብይት መፈጸሚያ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር “ዱቤ አለ” የተሰኘ ተለምዷዊውን ዱቤ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የሚያቀርብ መተግበሪያ በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ በይፋ አስመርቋል።

“ይህ ዱቤ” አለ የተሰኘው ይህ መተግበሪያ የዳሽን ባንክ ደንበኛ የሆኑ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ተገልጋዮች ከሚሰሩበት መስሪያቤት ቤት ስለ ሥራቸውና ደሞወዛቸው የሚገልጽ ደብዳቤ በማጻፍ ተመጣጣኝ ብድር የሚያገኙበት ዘዴ ነው።

በተመሳሳይ በግል ሥራ የሚተዳደሩ ደግሞ ንግድ ፈቃዳቸውና ህጋዊ የገቢ ማስረጃዎችን በማቅረብ ዱቤ ማግኘት ይችላሉ። ለዚህም ተገልጋዮች በአቅራቢያቸው በሚገኝ ዳሽን ባንክ በማመልከት ተጠቃሚ መሆን ያስችላቸዋል።

ተገልጋዮች ዛሬ ለሚገዙት እቃ የአገልግሎት ክፍያውን በ3 ወር፣ በ6ወር፣ በ12 ወር መክፈል የሚችሉ ሲሆን ለዚህም ላገኙት የእፎይታ ጊዜም ተመጣጣኝ ክፍያ የሚከፍሉ ይሆናል። በተጨማሪም አገልግሎቱ ከሞባይል መተግበሪያ በተጨማሪ በስልክ ቁጥራቸውና በሚሰጣቸው DubeAle ID መሰረት መጠቀም ይችላሉ።

ይህ አገልግሎት ለየት የሚያደርገው ተጠቃሚዎች ለሚያገኙት የዱቤ አገልግሎት የሚፈልጉትን አገልግሎት ይሸምቱበታል እንጂ በጥሬ ገንዘብ መቀየር ወይም ገንዘብ ወጪ ማድረግ አይቻልም።

ይህ መተግበሪያ ከተጠቃሚዎች በተጨማሪ ማንኛውም አገልግሎት አቅራቢዎች ሰጪዎች ተመዝግበው ምርትና አገልግሎታቸውን መሸጥ ይችላሉ ተብሏል።

ባንኩ ለእያንዳንዱ ደንበኞች የዱቤ ገደብ (Spending Limit) የሚያስቀምጥ ሲሆን በዚህ መሰረት ለጊዜው የተፈቀደው የዱቤ ጣሪያ እስከ 700,000 ብር መሆኑ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe