ድምጻዊት ትዕግስት ሳቂታ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሰርታ ተወዳጅነትን ያተረፈች ድምጻዊት ናት፡፡ ከዚህ አልበም ውጭ ለአድማጭ ያደረሰችውና ተቀባይነትንም ያገኘችበትን አልበም አልሰራችም፡፡ በርግጥ በምትኖርበት አገር ከውጭ ዜጎች ጋር በመሆን ሙዚቃ የሰራች ቢሆንም፤ብዙ እንዳልተደመጠ ገልጻለች፡፡
ትዕግስት በቀለ ላለፉት 20ዓመታት ኑሮዋ በጣሊያን ነው፡፡
በኤሌክትራ አሳታሚ ድርጅት ታትሞ በተሰራጨውና ለእርሷም የመጀመሪያዋ ስራ በነበረው ሳቂታው አልበም በወቅቱ 50ሺ ብር እንደተከፈላትም አስታውሳለች፡፡ ያልወጣ ሁለተኛ አልበም እንዳላትም ከኢትዮፒካሊንክ ጋር በነበራት ቆይታ ላይ ተናግራለች፡፡
ድምጻዊቷ ከረጅም ዓመታት በኋላ ኢትዮጽያ የተመለሰችው መስከረም ሦስት የ90ናዎቹ ድምጻዊያን ያቀርቡታል በተባለው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ስራዎቿን ለማቅረብ እንደሆነ ተናግራለች፡፡//

