ድምጻዊ አብዱ ኪያር በከዘራ መራመድ ጀመረ

በቅርቡ ሊፍት ወድቆበት አደጋ አጋጥሞት የነበረው ተወዳጁ ድምጻዊ አብዱ ኪያር አልሃምዱሊላሂ በከዘራ መራመድ ጀምሪያለሁ፤ደግሞም ተጽናንቻለሁ ብሏል፡፡ አብዲ ኪያር ያለበትን የጤንነት ደረጃ በቪዲዮ ቀርጾ በግሉ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርቷል፡፡

በቅርቡም ያለከዘራ መራመድ ተለማምጄ ያለምንም እርዳታ መጀመር እችላለሁም ብሏል፡፡

በደረሰብኝም ሀዘን በአካል፡በስልክ፡በኢሜልና በተለያየ መንገድ ያፅናናችሁኝ ፡ያበረታችኝ እና የፀለያልችሁኝ ወንድም እና እህቶቼ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ በማለት ለአድናቂዎቹ መልዕክቱን አስተላፍፏል፡፡

ተወዳጁ ድምዊ አብዱ ኪያር የዛሬ ወር ገደማ ሊፍት ወድቆብኝ ከከባድ አደጋ ተረፍኩ ባለ ቀናት ልዩትነት ውስጥ፤የእናቴን ሞት ተረዳሁ፡ፈተናው በዛብኝ፡ሁላችሁም በጾማችሁና  በፀሎታችሁ አስታውሱኝ ማለቱ ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe