ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ለቀው ወጡ፡፡
ትራምፕ ላለፉት አራት አመታት የቆዩበትን ቤተ መንግስት በይፋ ለቀው የመጨረሻ ስንብታቸውን ወደ ሚያደርጉበት አምርተዋል፡፡
ከስንብታቸው በኋላም ወደ ፍሎሪዳ የሚጓዙ ይሆናል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከባለቤታቸው ጋር ቤተ መንግስቱን ለቀው ሲወጡ፥ ምክትላቸው ማይክ ፔንስ በባይደን በዓለ ሲመለት ላይ ለመገኘት በስፍራው ቀርተዋል፡፡
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካሚላ ሃሪስ ምሽቱን በይፋ ቃለ መሃል እንደሚፈፅሙ ይጠበቃል፡፡
ወደ 25 ሺህ ወታደሮችም በዓለ ሲመቱን ያጅባሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡