ዶክተር እስራኤል ደገፋ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት ‎ ሆነው ተመረጡ

‎የኢትዮጵያ ቡና ጠቅላል ጉባኤ ሰሞኑን  ተደርጓል፤ ሲጠበቅ የነበረው የስራ አመራር ቦርድ ምርጫ  በመመሪያው መሰረት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት የሚሆነው “ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ” ከተወከሉ ሦስት ሰዎች ውስጥ ነው ። ‎በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርት አይሶሴሽን ወይም ከቡና ላኪ የተወከሉት ‎ አቶ ይስማሸዋ ስዩም፤‎ አቶ እክሊሉ ካሳና‎ ዶክተር እስራኤል ደገፋ ሲሆኑ
‎ከነዚህም ሦስት ውስጥ የኢትዮጵያ ቡና ፕሬዝዳንት ዶክተር እስራኤል ደገፋ ሆነው ተመርጠዋል።መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ስልጣናቸውን በክብር ለተተኪው አመራር አስረክበዋል ።ዶክተር እስራኤል የአንጋፋው ቀርጫንሼ ትሬዲንግ ዋና ስራስኪያጅ መሆናቸው ይታወቃል።
ስለ ዶክተር አስራኤል ደገፋ፦
አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና ፕሬዝዳንት ዶ/ር እስራኤል ደገፋ በሲዳማ ክልል በጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ ይርጋዓለም ከተማ ተወልዶ የንግድ ስራን ከትምህርቱ ጎን ለጎን ከአባቱ ከአቶ ደገፋ ስሜ ጋር አብሮ በመሆን ነበር የጀመረው። በተለይም የቡና ስራ ላይ ከልጅነት ጀምሮ የቡና ዝግጅት ሂደቱ እና የአርሶ አደሩ የጥቅም ማነስ እና እንግልትን ዘወትር እያየ በማደጉ ቁጭት ውስጥ በመግባት የቤተሰቡን ስራ እየሰራ ነገን በትልቁ ያልም ነበረ። ቡናን በኪሎ እየገዛ ቤተሰቡ ባለው የጭነት መኪናዎች ወደ አዲስ አበባ በመላክ ሀ ብሎ የጀመረው እስራኤል ዛሬ ላይ ላለበት ደረጃ የትላንቱ የአባቱን ጉያ መከተሉ ለትልቅ ደረጃ መድረሱ ምክንያት እንደሆነ በተለያየ መድረኮች ላይ ይናገራል ።
ዶ/ር እስራኤል ደጋፋ የአርፋሳ ጄኔራል ትሬዲግ ባለቤት የሆኑት (የአቶ ደገፋ ስሜ ) ልጅ ሲሆን ወላጅ አባቱ በቡና ስራ ላይ ከሶስት አስርት አመታት በላይ በካበተ ልምድ በዘርፉ ቆይተዋል። አባቱ ትምህርቱ ላይ እንዲያተኩር ግፊ ቢያደርጉበትም እርሱ ግን እለት እለት በአዲስ የስራ መንፈስ ከትምህርቱ ጋር ስራውን ያስኬድ ነበር።
ከወላጅ አባቱ ጋር አብሮ የቡና ስራን ይሰራ የነበረው ዶ/ር እስራኤል በሀገራችን ከፍተኛ የቡና ላኪዎች መካከልም አንዱ ነው። በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያው የሆነው እና ሙሉ ለሙሉ በማሽን ለቀማ የሚደረግለት በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጉብኝት ተደርጎ አድናቆት ያገኘው በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የሚገኘው ቀርጫንሼ ዘመናዊ የቡና እርሻን ጨምሮ በሀገራችን ባሉ በሁሉም የቡና አብቃይ አካባቢዎች የራሱ የቡና እርሻ እና የቡና ማዘጋጃ ሳይቶች ፣ ዘመናዊ የቡና ማበጠሪያ ማሽኖች ፣ የመኪና መገጣጠሚያዎች ፣ ቡና እስክሪቢቶ ፣ ቡና ፕሌት እና ሌሎች ትልልቅ ተቋሞችን በዚህ በወጣትነት እድሜው ላይ በባለቤትነት እየመራ ይገኛል።
ከ London School of management and technology ዶክተሬታቸውን የወሰዱት ዶ/ር እስራኤል ደገፋ በቢዝነሱ ዘርፍ የተለያዩ ሽልማቶችን በሀገራችን ፣ በአፍሪካና እና በአለም አቀፍ ደረጃ መሸለም ችለዋል። በሰላሳዎቹ መጨረሻ እድሜ ላይ የሚገኘው ዶ/ር እስራኤል ደገፋ ወደ ስፖርቱ ብቅ ማለቱ ምን አልባት የሀገራችን ኩራት የሆነው ቡናን ከማስተዋወቁ በተጨማሪ ይህን ህዝባዊ ክለብ ወጣት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ስፖርቱ ላይ አዲስ ነገር ይዘው ብቅ እንደሚሉ ይታመናል። በተለይም በታላቅ ደጋፊዎቹቹ የሚታወቀውን የኢትዮዽያ ቡናን ስፖርት ክለብ ደጋፊዎችም ትልቅ ብራንድ እንደሚሆን ይጠበቃል። አባቱ አቶ ደገፋ በይርጋለም ከተማ የራሳቸው ህንፃ ያላቸው ሲሆን በሲዳማ ክልል ሻፊና በምትባል ገጠር መንደርም ጤና ጣቢያ አስገንብተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe