ጀነራል /አምባሳደር ባጫ ደበሌ ተሾሙበት ሀገር አልታወቀም፤

በትላንትናው ዕለት ከተሾሙት አምባሳደሮች የተወሰኑት፤ ተቀማጭነታቸው በሀገር ውስጥ እንደሚሆን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፤

ጀነራል /አምባሳደር ባጫ ደበሌ ተሾሙበት ሀገር አልታወቀም፤

በፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በትላንትናው ዕለት ከተሾሙ 27 አምባሳደሮች ውስጥ የተወሰኑት ወደ ተሾሙበት ሀገር ሳይሄዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ አምባሳደሮች (non-resident ambassadors) እንደሚሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ፤ ሹመቱ “ዲፕሎማሲያዊ ሙያን መሰረት ያደረገ ነው” ብለዋል።

ቃል አቃባዩ ዛሬ ሐሙስ ጥር 19 በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫቸው፤ የአምባሳደሮች ሹመት የተከናወነው “በጥናት” መሆኑን ተናግረዋል። ሹመቱ ሶስት አሰራሮችን የተከተለ መሆኑን ለጋዜጠኞች የተናገሩት ዲና፤ ከእነዚህ መካከል አንደኛው አምባሳደሮች ወደ ተወከሉበት ሀገር ሳይሄዱ ነዋሪነታቸው በሀገራቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

“Non-resident አምባሳደር የሚባል አለ ያሉት አምባሳደሩ እዚሁ ሀገር እየኖሩ  የተወከሉበት ሀገር አስፈላጊ ሲሆን  ብቻ እየተመላለሱ የሚሰሩ non – resident ambassadors ናቸው” ሲሉ ከትላንቱ ተሿሚዎች ውስጥ የተወሰኑት ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

በዛሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ወደ ተወከሉበት ሀገር የማይሄዱ አምባሳደሮች ብዛት ምን ያህል እንደሆነ ጥያቄ ቢነሳም፤ ዲና ሙፍቲ ጥያቄውን ምላሽ ሳይሰጡ አልፈውታል። ትላንት ከተሸሙት አምባሳደሮቹ መካከል ጀኔራል ባጫ ደበሌ የት ሀገር እንደተሾሙ ያልታወቀ ሲሆን ዝርዝሩን በተመለከተ  ቃል አቀባዩ፤ “ገና እየተሰራ ነው” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘግቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe