ጂም ራትክሊፍ የማንቸስተር ዩናይትድን 25 በመቶ ድርሻ ገዙ!

ብሪታንያዊው ቢሊየነር ጂም ራትክሊፍ የማንቸስተር ዩናይትድን 25 በመቶ ድርሻ ወይም አክሲዮን ለመግዛት ስምምነት ተፈራረሙ።ራትክሊፍ ከግሌዘር ቤተሰቦች ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት በክለቡ 300 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስት ያደርጋሉ ተብሏል።ይህም ውጤት የራቀውን ክለብ ወደቀደመ ክብሩን በመመለስ ትርፋማ እንደሚያደርጋቸው ታምኖበታል።ብሪታንያዊው ቢሊየነር ጂም ራትክሊፍ የማንቸስተር ዩናይትድን 25 በመቶ ድርሻ ወይም አክሲዮን ለመግዛት ስምምነት ተፈራረሙ።

ራትክሊፍ ከግሌዘር ቤተሰቦች ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት በክለቡ 300 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስት ያደርጋሉ ተብሏል።ይህም ውጤት የራቀውን ክለብ ወደቀደመ ክብሩን በመመለስ ትርፋማ እንደሚያደርጋቸው ታምኖበታል።የሰር ጂም ራትክሊፍ ኩባንያ “ኢኒዮስ” የማንቸስተር ዩናይትድ ክለብን አስተዳደር ስራዎች ተረክቦ እንደሚሰራም ተገልጿል።

“ከልጅነቴ ጀምሮ እየደገፍኩት ከኖርኩት ማንቸስተር ዩናይትድ ቦርድ ጋር በአስተዳደር ስራዎች በጋራ ለመስራት በመስማማታችን ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛል” ብለዋል ራትክሊፍ።የክለቡን ውጤታማነት ለመመለስም ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይና እውቀትን እንደሚጠይቅ በመጥቀስ ድርጅታቸው በተለያዩ ሊጎች ያካበተውን ልምድ በኦልትራፎርድ እንደሚተገብር ነው ያብራሩት።

ቢሊየነሩ የስምምነት ውሉ እንደተጠናቀቀ 200 ሚሊየን ዶላር፤ እስከ 2024 መጨረሻ ደግሞ 100 ሚሊይን ዶላር ለክለቡ ይከፍላሉ።የግሌዘር ቤተሰቦች በህዳር 2022 ዩናይትድን ለመሸጥ ፍንጭ ከሰጡ በኋላ ከራትክሊፍ ጋር ክለቡን ለመግዛት ሲፎካከሩ የቆዩት ኳታራዊው ሼክ ጃሲም ቢን ሃማድ አል ታኒ ከፉክክሩ መውጣታቸውን አስታውቀዋል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe