ጃፓን እና ቻይና በታይዋን ጉዳይ መነጋገር ጀምረዋል፡፡ አዲሷ የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ቻይና በታይዋን ላይ ወረራ የምትፈጽም ከሆነ የጃፓን ህልውልና አደጋ ላይ ይወድቃል ብለዋል፡፡
ቤጂንግ ይህን አይነቱን የቶኪዮን አካሄድ አደገኛ እና ስህተት ስትል ጠርታዋለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ ቻይና በታይዋን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ተከትሎ የጃፓን ምላሽ ምን እንደሚሆን ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ነገርየው ውጥረት ቀስቃሽ ሆኗል፡፡
እንዲህ አይነቱ ጥቃት የጃፓንን ህልውና የሚፈታተን እንደሚሆን ነው ምላሽ የሰጡት፡፡ ቻይና የጠቅላይ ሚኒስትሯ ንግግር ስህተት ከመሆኑም በላይ ለታይዋንም ልክ ያልሆነ መልዕክት ነው ያስተላለፉት ብላለች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ወደ ስልጣኑ ከመጡ ጥቂት ሳምንታት ብቻ የሆናቸው ቢሆንም፤የቻይናውን ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግን በደቡብ ኮሪያ ከሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የኤፔክ ጉባኤ ላይ አግኝተዋቸዋል፡፡
ከሰሞኑም ከታይዋን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል፡፡ እነዚህ መገናኘቶች ጃፓን እንዴት ዲፕሎማሲዋን ሚዛናዊ ለማድረግ እያጠራች እንደሆነ የሚያመላክት ነው፡፡//

