ጆ ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር የሚመክር የዴሞክራቶች ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ ላኩ

በትግራይ ክልል ባለው ጉዳይ ዙሪያ ይመክራል የተባለለት ልዑክ በዴሞክራቱ ሴናተር ክሪስ ኩን ይመራል ተብሏል!

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በትግራይ ክልል ባለው ጉዳይ ዙሪያ የሚመክርና በዴሞክራቱ ሴናተር ክሪስ ኩን የሚመራ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ ላኩ።

የፕሬዝዳንቱ የቅርብ የኮንግረስ አጋር እንደሆኑ በሚነገርላቸው በሴናተር ክሪስ ኩን የተመራው ልዑኩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኝቶ ይመክራል ተብሏል፡፡

ባይደን “በክልሉ ስላጋጠመው ሰብዓዊ ድቀት እና የመብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዲሁም ሁኔታው በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሊደቅን ስለሚችለው የጸጥታ አደጋከፍተኛ ስጋት” ገብቷቸው እንደ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪያቸው ጃክ ሱሊቫን ገለጻ፡፡

በክሪስ ኩንየተመራው ልዑክም ይህንኑ የፕሬዝዳንቱን ስጋት ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ገልጾ እንደሚወያይም ይጠበቃል።

በተጨማሪም ሴናተር ክሪስ ኩን ከአፍሪካ ህብረት የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩም ተጠቁሟል።

የዴላዌር የዴሞክራቶች ተወካይ የአዲስ አበባ ጉዞ አዲሱ የባይደን አስተዳደር በትግራይ ያጋጠመውን ችግር በተመለከተ ያለውን ስጋት ደጋግሞ መግለጹን ተከትሎ የሚደረግ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒዮ ብሊንከን ምናልባትም እስከ “ዘር ማጽዳት”ሊደርሱ የሚችሉ ወንጀሎች ተፈጽመው ሊሆን እንደሚችል በመጠቆም ጉዳዩ እንዲጣራ እና ጥፋተኞች ተጠያቂ እንዲሆኑ ማሳሰባቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሆኖም ኢትዮጵያ ማሳሰቢያውን ክፉኛ በመተቸት ተቃውማለች፡፡

አሜሪካ በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ፤ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ሰብአዊ እርዳታዎችን ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።

አሁንም የተፈጠረውን ችግር ለማቃለል የሚያስችል የ52 ሚልየን የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ እንደምታደርግም በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል ማስታወቋ የሚታወስ ነው፡፡

አሜሪካ አስካሁንም ለትግራይ ክልል በአጠቃላይ የ153 ሚልየን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe