ግሎባል አሊያንስ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

“ግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያን መብቶች” በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የግሎባል አሊያንስ መስራች አርቲስት ታማኝ በየነ በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ምክንያት በግፍ ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፉን አስረክቧል።

ድጋፉ ምግብ ነክ፣ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ የሆኑ ግብዓቶችን ያከተተ ነው።

አርቲስት ታማኝ በቀጣይ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው በአፋርና ጎንደር ለሚገኙ ዜጎችም ድጋፉ ተደራሽ እንደሚሆን ጠቅሷል።

ድጋፉ ከ”CRVPF”(Children’s Right and Violence Prevention Fund) ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በትብብር የቀረበ እንደሆነ ተገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ኮማንድ ፖስት የሕብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ አስተባባሪው እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሡ ጥላሁን ግሎባል አሊያንስ ለተፈናቃዮች ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe