ግብጽ እና ሳውዲአረቢያ የጋራ የጦር ልምምድ ማድረግ መጀመራቸው ተሰማ

ግብጽ እና ሳውዲአረቢያ የጋራ የጦር ልምምድ ማድረግ መጀመራቸው ተሰማ፡፡ በመስከረም ወር አካባቢ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግብጽና ሳውዲ በቀይ ባህር ላይ የጋራ የባህር ሃይል የመገንባት እቅድ አላቸው፡፡

ሬድ ዌቭ 8 በተባለው በዚህ የጋራ የጦር ልምምድ ግብጽና ሳውዲን ጨምሮ ሌሎች የቀጠናው ሀገራትም እንዳሉበት ታውቋል፡፡

ከሁለቱ ሀገራት በተጨማሪ የዮርዳኖስ፡የሱዳን፡የየመን እና የጅቡቲ ባህር ሃይሎችም በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

ሀገራቱ በዓለም ላይ ተዋቂ በሆነው የንግድ መስመር ላይ ነው ልምምድ የጀመሩት፡፡ ልምምዱ ኢትዮጽያ የባህር በር ለማግኘት በህጋዊ መንገድ ጥያቄዎችን እያቀረበች ባለበት ስዓት መሆኑ ደግሞ ለጉዳዩ ክብደት ሰጥቶታል፡፡

ግብጽ ኢትዮጽያን በቀይ ባህር ጉዳይ በዲፕሎማሲም፡በኢኮኖሚም ተጠቃሚ እንዳትሆን ጥረት በማድረግ ላይ እንደምትገኝ በኢትዮጽያ ውጭ ጉዳይ በኩል በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ይሔው የቀይ ባህር የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የቀይ ባህር ወዳጅ ሀገራት የሚባለው ጥምረት በግብጽ እና በሳውዲ የተመሰረተ በኋላም  ኤርትራ፡ሱዳን፡ሶማሊያ፡ጅቡቲ፡ዮርዳኖስ እና የመን የተቀላቀሉበት ነው፡፡ ልምምዱ ለቀናት ያህልም እንደሚዘልቅ ዘኒው አረብ አስነብቧል፡፡

እነዚህ ሁሉም ሀገራት ቀይባህርን ከህንድ ውቂያኖስ እና ስዊዝ ካናል የሚያገናኘውን ዳርቻ የሚጋሩ ናቸው፡፡

ይህ የንግድ መስመር ኤዢያን፡መካከለኛው ምስራቅን እና አውሮፓን የሚያገናኝ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ቀጠናው የዓለም አቀፍ ወታደራዊ ሃይል ማሳያም ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

የዚሁ ጥምረት አካል የሆነችው ጅቡቲ ለዩናይትድ ስቴትስ፡ፈረንሳይ፡ቻይና እና ጃፓን ወታደራዊ መሠረት መሆኗም ይታወቃል፡፡

የቀይ ባህር ጥምረት ሀገራት ከ2019 ጀምሮ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፤ነገር ግን ጥምረቱ የቀጠናውን ዋና ተዋናዮች የሆኑትን ኢትዮጽያን እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኢምሬቶችን ያካተተ አይደለም፡፡

የየመኑ አማጺ ሃይል ሁቲ የጋዛው ጦርነት ከተነሳበት 2023 አንስቶ ንብረትነታቸው የእስራኤል በሆኑ እና ከእስራኤል ጋርም ግንኙነት አላቸው በሚላቸው የንግድ መርከቦች ላይ በቀይ ባህር ሚሳኤል ሲያስወነጭፍ ቆይቷል፡፡

በኢራን የሚደገፈው ሁቲ በቀይ ባህርና በአረቢያን ባህር ላይ በንግድ መረከቦች ጥቃት የሚፈጽመው ለጋዛው ሃማስ ድጋፉን ለማሳየትና በእስራኤል ላይ ጫና ለመፍጠር በሚል ነው፡፡

ዋሸንግተን እና የየመኑ ሁቲ ቡድኑ በመከርከቦች ላይ ጥቃት እንዳያደረስ በሚል መስማማታቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጋዛው ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ ግን እርሱም በቀይ ባህር ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እንደሚቀጥል ነው ቃል የገባው፡፡

ሳውዲያ አረቢያ በሰነዓ መሠረቱን ያደረገውን የሁቲውን አስተዳደር እውቅና የማትሰጠው ሲሆን፤በምትኩ በኤደን መቀመጫውን ላደረገውና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና ለተሰጠው መንግስት ነው የምትደግፈው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe