ግብጽ የዓባይ ውሃ በመጠቀም የበረሃ ከተማ ልትገነባ ነው

ግብጽ የዓባይ ውሃ አጠቃቀምን በሰባት በመቶ የሚያሳድግ የበረሃ ከተማ ልትገነባ ነው፡፡

ግብጽ በዓባይ ውሃ አሁን እየተጠቀመች ካለው የውሃ መጠን ሰባት በመቶ በላይ ተጨማሪ ውሃ የሚፈልግ የበረሃ ከተማ ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጓ ተሰማ፡፡

የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞስታፋ ማድቡሊ ትናንት ፕርጀክቱን ይፋ ማድረጋቸው በመገናኛ ብዙሃን ተዘግቧል፡፡ የሚገነባው የበረሃ ከተማ ከካይሮ 42 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ጂሪያን ከተማ አቅራቢ እንደደሆነ ተነግሯል፡፡

ፕሪጀክቱ ግብጽ ከዓባይ ወንዝ ከምታገኘው ኢ ፍትሐዊ የውሃ አጠቃቀም ከሰባት በመቶ በላይ ፍጆታ ያለው ሲሆን መጠኑም አራት ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

የበረሃ ከተማ ፕሮጀክቱ አዲስ የእርሻ ልማትንም ያካተተ ሲሆን ሁለት ነጥብ 28 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆን እርሻ የሚጀመርበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ለከተማዋ የሚቀርበውን የዓባይ ወንዝ ውሃን በመጥለፍ በመስታወወት በሚሰሩ መተላላፊያ ቤቶች ውስጥ የሚጓጓዝ ሲሆንበየቀኑ 10ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ያህል ውሃ እንዲያደርስ ታቅዷል፡፡/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe