ግብፅ በሜዲትራኒያን ባሕር 5.7 ቢሊዮን ኩብ ሜትር የያዘ  የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አገኘች 

🇪🇬 ግብፅ በሜዲትራኒያን ባሕር ባካሄደችው የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማግኘቷንና በፍጥነት ምርት ማውጣት ለመጀመር ማቀዷን የሀገሪቱ የፔትሮሊየም እና የማዕድን ሀብት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦ 

✔️የጋዝ ክምችት፦ 5.7 ቢሊዮን ኩብ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ይዟል ተብሎ የተገመተ ሲሆን ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለውን የተጣራ መጠን ለመወሰን ጥናቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

✔️አዲስ የማስተላለፋያ መስመር ፦ የጋዝ ማውጣት ሂደቱን ለማፋጠን የጋዝ ጉድጓዱን ከነባር የመሠረተ-ልማት አውታር ጋር የሚያገናኝ 22 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ታቅዷል።

✔️ተጨማሪ የፍለጋ ሥራዎች፦ እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ ከሆነ የተሻሻሉ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች እና ያልተከፈሉ ውዝፍ ክፍያዎች ለአጋሮች መከፈላቸው ተጨማሪ የፍለጋ ሥራዎችን ለማካሄድ መነቃቃትን ፈጥሯል።

Sourcesputnik

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe