ግብፅ ዩቲዩበሮችን ግብር እንዲከፍሉ ውሳኔ አስተላለፈች

የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ገቢ የሚያገኙ ዜጎችን ቁጥር መጨመር ተከትሎ የግብፅ የግብር ባለስልጣን መስርያ ቤት ዩቲዩበሮች ዓመታዊ ገቢያቸውን እንዲያስመዘገቡ፣ እንዲያሳውቁ እና ግብር እንዲከፍሉ ውሳኔ አማሳለፉ ተሰምቷል።

የመንግስት የግብር ውሳኔ በዋናነት ትኩረት ያደረገዉ በየዓመቱ ከ32,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ በሚያገኙት ዮቲዮበሮችና ጦማሪያንን እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ ዜጎች ድጋፍ እና ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

የግብጽ የታክስ ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሀላፊ መሐመድ አል ጌይርን በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ “ግብፅ ውስጥ ትርፍ የሚያገኝ ማንኛውም ሰው የሥራው መስክ ምንም ይሁን ምን በትክክል ግብር ሊከፍል ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከፈረንጆቹ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የግብፅ ባለስልጣናት ከ50,000 በላይ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠቃሚዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ የጀመሩ ሲሆን “የተሳሳተ መረጃ” ለጥፈው በተገኙት ላይ ክስ ሲመሰርቱ ቆይተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe