ጎሕ ቤቶች ባንክ ለባለአክሲየዮኖች የሚሰጠው ትርፍ 0.24 ሳንቲም መሆኑ ተሰማ

7 ሺ ያህል ባለአክሲዮችን ይዞ ስራ የጀመረው ጎሕ ቤቶች ባንክ ዛሬ በኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል ባካሄደው የባለአክሲዮኖች አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ባንኩ አትራፊ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን የትርፍ ክፍፍሉ ግን እስከዛሬ ድረስ ከነበሩት ባንኮች ትርፍ እጅግ አነስተኛ መሆኑ ተገልፃል፤
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ታዋቂው ኢኮኖሚስት አቶ ጌታሁን ናና የቀረበው የባንኩ የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈፃጸም ላይ እንደተገለፀው ጎሕ ቤቶች ባንክ የመኖሪያ ቤትን ችግር ለመቅረፍ የቤት መግዢ ማደሻና መስሪያ የሚሆን ብድር ላይ አተኩሮ የሚሰራ መሆኑን አስታውቀው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 7ሚሊየን 934 በር ማትረፉን ተናግረዋል፤
ባንኩ ስራ ከጀመረ ስምንት ወር ብቻ  መሆኑን የገለፁት አቶ ጌታሁን በተመሰረተና ስራ በጀመረ ዓመት ሳይሞላው ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉ ዘርፉ በስፋት ከተሰራበት ተስፋ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፤
ባንኩ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ 256 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ከ298 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠት መቻሉን ታውቋል፤

ባለፈው ዓመት 7.934 ሚሊዮን ብር ያተረፈው ጎሕ ቤቶች ባንክ የብሔራዊ ባንክ ያወጣው ህጋዊ መጠባበቂያና ግብር ተቀንሶ ለባለ አክሲዮኖች የሚደርሰው ትርፍ ድርሻ 0.24 ሳንቲም ስለሆነ ገንዘቡን ለባለአክሲዮችኖች ከማከፋፈል ይልቅ ለትርፍ ግብር መጠባበቂያ እንዲውል መወሰኑ ታውቋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe