ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ ነገ ወደ ዋሽንግተን እንደሚያቀኑ ተሰማ፡፡ እረቡ እለትም ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በኢራን ጉዳይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረብ እለትም ወደ እስራኤል ይመለሳሉ ተብሎ እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ስለ ሰሞንኛው የኢራን እና የአሜሪካ ንግግር ጉዳይ ለመወያየት እንደሆነም ተዘግቧል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዋሽንግተኑ ጉዞ ይደረጋል ተብሎ እቅድ ተይዞ የነበረው በመጭው ሳምንት እንደነበር የዋይት ሐውስ ባለስልጣናት ገልጸው በድንገት ወደዚህ ሳምንት እንዲመጣ መደረጉ አክሲዮስ ለተሰኘው የዜና ምንጭ ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ ነገ የአሁነኛውን ጉዞ ጨምሮ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዳግም ወደ ዋይት ሐውስ ከተመለሱ ባለፉት 12 ወራቶች ውስጥ ሰባተኛ ጉዟቸው መሆኑን ታይምስ ኦፍ እስራኤል ጽፏል፡፡ የቀርብ ጊዜ ጉዞዟቸው የነበረውም ባለፈው ታህሳስ የገና ዋዜማ በዓል ሲሆን ከፍሎሪዳ ማራ ላጎ ሪዞርት ነበር የተገናኙት፡፡
አሜሪካ እና ኢራን አርብ እለት በኦማን ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ እና አማቻቸው ኩሽነር ከኢራን ተወካዮቻቸው ጋር በኦማን ለስምንት ስዓት ያህል ማሳለፋቸው ተነግሯል፡፡
እስራኤል አሜሪካ ከኢራን ጋር እያደረገችው ባለው ድርድር ኢራን ከኒውክሌር ፕሮግራሟ በተጨማሪ በባላስቲክ ሚሳኤሎቿ ዙሪያ እና በቀጠናው ስለምታስታጥቃቸው የውክልና ተዋጊዎቿ ጉዳይም ከስምምነት መደረስ አለበት የሚል እምነት አላት፡፡
ኢራን ደግሞ በኒውክሌር ፕሮግራሜ ዙሪያ ንግግር ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ነገር ግን በባላስቲካ ሚሳኤል ጉዳይ አትምጡብኝ እሱ ቀይ መስመሬ ነው የሚል አቋም አላት፡፡
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አባስ አራግቺ ዩናይትድ ስቴትስ ለመዋጋት ዝግጁ ከሆነች እኛም ዝግጁ ነን ማለታቸውን የእስራኤሉ አይ ኤል ቲቪ ዘግቧል፡፡
አሜሪካ በቀጠናው እያንቀሳቀሰች ያለው ሃይል እኛን አይስፈራንም መታወቅ ያለበት እኛ የዲፕሎማሲ ህዝቦች ነን ግን በዚያው መጠንም ለጦርነቱ እየተዘጋጀን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ
የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊት ኮቭ እና ኩሽነር ከኦማኑ የአርቡ ድርድር በኋላ USS የአብርሃም ሊንከን የጦር መርከብ ተሸካሚ የሆነችውን ግዙፍ አውሮፕላን መጎብኘታቸው ታውቋል፡፡
ይች የጦር መርከብ ወደ ቀጠናው መድረሷን ተከትሎ በኢራን እና በአሜሪካ መካካል ያለው ግንኙነት ወደ ውጥረት እንዲገባ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፡፡
ይችው የጦር መርከብ ተሸካሚ አውሮፕላን የምትገኘው በአረቢያን ባህር ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የአሜሪካ ተደራዳሪ የሆኑት ዊትኮቭ እና ኩሽነር ለሁለተኛ ጊዜ በቀጣይ ሳምንት ከኢራን ተደራዳረዎች ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአርቡን ድርድር በጣም ጥሩ ነበር ሲሉ ጠርተውታል፡፡
አርብ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የደተረገው ድርድር ከሰኔው ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ነው፡፡//

