‹ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ በጣም ያውቁኛል ብዬ መናገር እችላለሁ› ዶ/ር  ብርሃኑ ነጋ

ስድስተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ  መስከረም 24 ስራ የጀመረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት የቀረበውን አዲስ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁን ተከትሎ አዳዲስ ሚኒስትሮችን በዛሬው ዕለት ሰይሟል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቅራቢነት ከተሾሙ 22 ሚኒስትሮች መሀከል ሶስቱ የተፎካካሪ ፖርቲ መሪዎች መሆናቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙ ግለሰቦች በፉክክር መንገድ ሳይሆን በትብብር መንፈስ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ገልፀው ‹ሌብነትንና ልመናን የሚፀየፉ  ሚኒስትሮች እንዲሆኑም› አሳስበዋል፡፡

‹ውጭ ሆኖ መንግስትን መተቸትና የመንግስትን ስልጣን ይዞ ለውጥ ማምጣት ብዙ ልዩነት አለው› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሚኒስትር ደረጃ የተፎካካሪ ፖርቲ አባላትን ያካተተትነው ብልፅግና ፖርቲ በምርጫው ዋዜማ ለህዝብ ቃል በገባው መሠረት እንደሆነ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ በሚኒስትረ ደረጃ የተሾሙት የተፎካካሪ ፖርቲ መሪዎች ሶስት ሲሆኑ የኢዜማ መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስቴር፤ የአብን ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም የኦነግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ከሹመትና ቃለ መሃል ስነ ስርዓቱ በኋላ ቁም ነገር መፅሔት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን አነጋግራለች፡ ዶ/ር ብርሃኑ እንዳሉት  ትምህርት ሚኒስቴር የረዥም ዓመት ታሪክ ያለው ነባር ተቋም መሆኑንና ለማንኛውም የዕድገት ለውጥ መሠረቱ ትምህርት መሆኑን በመገንዘብ የተቻለኝን ያህል ለውጥ ለማምጣት እጥራለሁ ብለዋል፡፡ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ዶ/ር ብርሃኑ ከትምህርት ሚኒስቴርነት ይልቅ በገንዘብ ሚኒስቴርነት ቢመደቡ የተሻለ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ብለው መግለፃቸውን መነሻ በማድረግ ጥያቄ ላቀረበችው ቁም ነገር መፅሔት ሲመልሱ  ‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ እሳቸውን በትምህርት ሚኒስቴርነት መመደባቸው እንዳስደሰታቸውና በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ያለኝን የረዥም ዓመት ልምድ መሠረት ያደረገ ይመስለኛል ›ብለዋል፡፡ የምክር ቤቱን አባላት ሀሳብ ውድቅ ያደረጉት ዶ/ር ብርሃኑ ‹በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደንብ ያውቁኛል ማለት ነው ለማለት እችላለሁ፡፡› ብለዋል፡፡

Parlama
Parlama

‹የትምህርት ስርዓቱን ለመቀየር እሰራለሁ› ያሉት ዶ/ር ብርሃኑ የትምህርት ስርዓቱ በሀብታምና በድሃ ልጆች መሀከል የትምህርት አሰጣጥ ልዩነት የፈጠረ በመሆኑ የድሃ ልጆችም ጥራት ያለው ትምህርት የሚያገኙበትን ስርዓት ለመዘርጋት ከሌሎች የሚኒስቴሩ የስራ ባልደረቦቼ ጋር እሰራለሁ ›ብለዋል፡፡

ለምርጫ ስትወዳደሩ ባቀረባችሁት የኢዜማ የትምህርት ፖሊሲና በብልፅግና የትምህርት ፖሊሲ መሀከል ልዩነት እንደነበር ይታወቃልና አሁን ይህንን ሹመት ሲቀበሉ የሚያስፈፁሙት የብልፅግናን ፖሊሲ ስለሚሆን ከእናንተ ፖሊሲ ጋር አይጋጭ ወይ በሚል ለቀረበላቸው ሌላ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ዶ/ር ብርሃኑ የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎችን የትምህርት ፖሊሲ ብንፈትሽ ትምህርትን በጥራት ለዜጎች ማዳረስን ትኩረት ያደርጋል ያሉት ሚኒስትሩ ‹በመሆኑም በትምህርት ጉዳይ ያን ያህል የሚያጋጭ ፖሊሲ የለንም ለማለት ይቻላል› ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቧቸውና በምክር ቤቱ የፀደቀው የካቢኔ አባላት ዝርዝር የሚከተለው ነው፡፡

 1. አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር
 2. ዶ/ር አብርሃም በላይ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር
 3. አቶ አህመድ ሽዴ የገንዘብ ሚኒስትር
 4. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የስራና ክህሎት ሚኒስትር
 5. አቶ ኡመር ሁሴን የግብርና ሚኒስትር
 6. ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር
 7. ዶ/ር ኢንጀነር ሃብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
 8. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቦንገር የትምህርት ሚኒስትር
 9. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ- የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር
 10. አቶ ገ/መስቀል ጫላ የንግድና እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር
 11. አቶ መላኩ አለበል የኢንደስትሪ ሚኒስትር
 12. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም አሸናፊ የሰላም ሚኒስትር
 13. ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የፍትህ ሚኒስትር
 14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር
 15. አቶ በለጠ ሞላ ጌታሁን- የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀረቡ
 16. አምባሳደር ናኒሴ ጫሌ- የቱሪዝም ሚኒስትር
 17. አቶ ላቀ አያሌው- የገቢዎች ሚኒስትር
 18. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ኢብራሂም-የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
 19. ታከለ ኡማ በንቲ- የማዕድን ሚኒስትር
 20. ዶ/ር ፍፁም አሰፋ- የፕላን ልማት ሚኒስትር
 21. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ-የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
 22. ቀጀላ መርዳሳ -የባህልና ስፖርት ሚኒስትር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe