ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የሰሜኑን ጦርነት በተመለከተ በፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠየቀ

በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበላቸው።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ያቀረቡት፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ወክለው የተወካዮች ምክር ቤትን የተቀላቀሉ አራት የፓርላማ አባላት ናቸው።
የፓርላማ አባላቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲጠሩላቸው የሚጠይቀውን ደብዳቤ ለተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ያስገቡት ባለፈው ዓርብ ጥቅምት12/ 2014 ዓ.ም. መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካል ምክር ቤት ቀርበው ምላሽ እንዲሰጡባቸው ከተጠየቁ ጉዳዮች መካከል፤ የኢፌዲሪ መንግስት “በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በምን ያህል ጊዜ የማጠናቀቅ” እቅድ እንዳለው ነው።
የፌደራል መንግስት ጦርነቱን ካጠናቀቀ በኋላ “በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎችን በምን ያህል ጊዜ ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየረራ እንደሆነ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያብራሩላቸው እንደሚፈልጉ የኢዜማ የፓርላማ ተመራጮች በደብዳቤያቸው በተጨማሪነት ጠይቀዋል።
አራቱ የፓርላማ አባላት የጦርነቱን “ዘለቄታዊ መፍትሔ” የተመለከተ ጥያቄም በደብዳቤያቸው አንስተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe