በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19ን አስመልክቶ የሚወጡ መረጃዎችን ሥርዓት ለማጠናከር የሚያስችል ፕሮቶኮል ተዘጋጀ
በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19ን አስመልክቶ የሚወጡ መረጃዎችን ሥርዓት ለማጠናከር የሚያስችል ፕሮቶኮል ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ መዋሉን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
Read also:የሕዳሴው ግድብ ዝቅተኛ የመደራደሪያ ነጥባችን የቱጋ ነው?
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የቀውስ ጊዜ መረጃ አሰጣጥ ፕሮቶኮል 2012 የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮቶኮሉ መረጃዎች በዘፈቀደ እና በተበታታነ መልኩ እንዳይሰጡ እና ዜጎች ትክክለኛ እና ወጥ የሆኑ መረጃዎችን ከአንድ ማዕከል ማግኘት እንድችሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሚኒስቴር መሥሪያቱ አስታውቋል።
ፕሮቶኮሉ ከላይ እስከ ታች በተናበበ እና በተማከለ አደረጃጀት በውጤታማነት ለመጠቀም የሚያግዝ ሲሆን የኮቪድ-19 መረጃዎችን በሥርዓት ለመሰብሰብ፣ ለማደራጀት እና ለመተንተን አልፎም ለሚመለከታቸው አካላት ለሚዲያ እና ለኅብረተሰቡ በተሟላ መልኩ በማሰራጨት የሚፈለገውን ግንዛቤ ለመፍጠርና ውጤት ለማምጣት እንደሚረዳ የተጠቆመው።
Read also:ወጣቷ ሚሊየነር የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለቤት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
የመረጃዎችን የትክክለኛ ምንጭነት፣ የቋንቋ አጠቃቀም ፣ የአቀራረብ እና የይዘት መርሆች እና ሌሎች ጉዳዮችን ፕሮቶኮሉ በዝርዝር ማካተቱም ተገልጿል።
ፕሮቶኮሉ በጤናው ሴክትር ከላይ እስከ ታች ባሉ የመዋቅር አደረጃጀቶች ኮቪድን በተመለከተ ለሚወጡ መረጃዎች ተግበራዊ የሚሆን ሲሆን በዝግጅት ሂደቱም የናሽናል ኮሙዩኒኬሸን ግብረ ኃይል፣ ክልልሎች እና የከተማ መስተዳደሮች እንዲሁም ኤጀንሲዎች እና ሆስፒታሎች የተሳተፉበት መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።