ፀሐይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥበትን የመጀመሪያ ቅርንጫፍ ከፈተ

ለደንበኞች ክፍት የሆነው ቅርንጫፍ ለባንኩ የመጀመሪያው የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጥ ነው። በመረሀ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ላለፉት ወራት ባንኩ ከወለድ ነፃ ተጠቃሚ ደንበኞቹን ሲያስተናግድ የነበረው ፈጅር በሚል ስያሜ በመስኮት ደረጃ እንደነበር የባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ተናግረዋል።

ከወለድ ነፃ ተጠቃሚ ደንበኞች የተለያዩ የተቀማጭ እና የኢንቨስትመንት የሂሳብ አይነቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል እንዲሁም በሚፈልጉት የሂሳብ አይነት ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መቆጠብ የሚችሉበት አማራጭ እንደቀረበ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ተናግረዋል።

ባንኩ “ፈጅር ቁባ” ቅርንጫፉን አጠና ተራ አካባቢ የከፈተ ሲሆን ከዚህ በኃላም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎች ለመክፈት እየሰራ መሆኑን ሰምተናል።

በመጭው ሳምንትም ፉሪ አካባቢ “ፈጅር አማና” በሚል ስያሜ ሁለተኛውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ እንደሚከፈት ሀላፊዋ ተናግረዋል።

ፀሐይ ባንክ ሀምሌ 16፣ 2015 ዓ.ም በ30 ቅርንጫፎች ስራ የጀመረ ሲሆን መደበኛውን እና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን እኩል የጀመረ ባንክ  ነው።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe