ፀሐይ ባንክ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊየን ብር ሊያድግ ነው

ፀሐይ ባንክ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊየን ብር ለማሳደግ ዛሬ በአንደኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መወሰኑ ተነገረ፡፡
የባንኩ ካፒታል 2 ቢሊየን 162 ሚሊየን 534 ሺህ ብር በመጀመር ወደ 5 ቢሊየን ብር እንዲያድግ ተወስኗል፡፡
ይህም የገንዘብ መጠን እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር 2024 ድረስ ተከፍሎ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ባንኮች ሊኖራቸው የሚገባው ዝቅተኛ የካፒታል መጠን ላይ ማሻሻያ በመደረጉ እና ይሄንኑ ማሻሻያ በተገቢው መልኩ ማሟላት አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡
የፀሐይ ባንክ ካፒታል አቅሙን በመጨመር ከሌሎች ባንኮች ጋርም ተወዳዳሪ ለማድረግ እንዲቻል እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
የውጪ ባንኮች በአገር ቤት ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቀድ ፖሊሲ በመውጣቱ በባንኮች ላይ በሚፈጠረው ውድድር አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ፀሐይ ባንክ የተሻለ የካፒታል ቁመና ላይ መገኘት አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታዬ ዲበኩሉ እንደገለጹት÷ባንኩ አገልግሎት የሚሰጡ ከ45 በላይ ቅርንጫፎች አሉት፡፡እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ወደ 100 ቅርንጫፎች ለማድረስ እንዲሁም የደንበኞቹን ቁጥር 356 ሺህ ለማድረስ ባንኩ እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ፀሐይ ባንክ የተፈረመ ካፒታል 2 ቢሊየን 837 ሚሊየን 466 ሺህ ብር ነው፡፡ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 865 ሚሊየን 976,500 ብር ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe