ፀሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ የክብር ዲፕሎማና እውቅና ተሰጠው!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በየዓመቱ በሚያዘጋጀው “ዝክረ ኪነጥበብ” ልዩ መርሃግብር በማዘጋጀት ለሀገራቸው ኪነጥበብ በሙያቸው የላቀ አስተዋጽኦ ካበረከቱ ጠቢባን አንዱን በመምረጥ የክብር ዲፕሎማና እውቅና ሲሰጥ ቆይቷል::
ዘንድሮውም በ2016 ዓ.ም “ዝክረ ኪነጥበብ” ፕሮግራምም የበርካታ ቴአትሮች ደራሲ ፀሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ የክብር ዲፕሎማና እውቅና ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገርፍቅር ቤት ተበርክቶለታል።
በእውቅናው ሥነሥርዓት ላይም በፀሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ ላይ ትኩረት ያደረገ ዘገቢ ፊልም ፣ በተውኔቶቹ ላይ በባለሞያ ዳሰሳና ከደፈረሱ ዓይኖች ቴአትር ላይ ቅንጫብ ተውኔት ቀርቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe