ፍልስጤማዊው የኦስካር ተሸላሚ ሐምዳን ባላል በይዞታ ስር ባለው ዌስት ባንክ በእስራኤል ወታደሮች መያዙን ፍልስጤማዊያን የመብት ተሟጋቾች ገለፁ፡፡
ኖ አዘር ላንድ የተባለውና በቅርቡ ኦስካር ያሸነፈው ፊልም አዘጋጁ ከሆኑት አራት ፊልም ሰሪዎች አንዱ የሆነው ሐምዳን ነው በቁጥጥር ስር ውሏል የተባለው፡፡
ሐምዳን ድብደባ ተፈጽሞበታል፤በአምቡላንስ ውስጥ ሳለም በእስራኤል ወታደሮች ተይዞ ተወስዷል ነው የተባለው፡፡
የእስራኤል መከላከያ ሃይል ሐምዳንን በስም ባይጠቅስም ሦስት ፍልስጤማዊያን እና አንድ እስራኤላዊ የፀጥታ ሃይሎች ላይ ድንጋይ በመወርወር ተጠርጥረው ተይዘዋል ብሏል፡፡//

